ክብር ፡ ላንተ ፡ እግዚአብሔር (Keber Lante Egziabhier)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

የእስራኤልን ፡ ህዝብ ፡ የተገዳዳረው
የፍልስጤም ፡ ጀግና ፡ ጦረኛው
ሲዘንጥ ፡ ሲፎክር ፡ ዳዊት ፡ ተመልክቶ
ወደ ፡ ሰልፉ ፡ ገባ ፡ በአምላኩ ፡ ተኩራርቶ
በአንድ ፡ ጠጠር ፡ ብቻ ፡ ጐልያድን ፡ ዘረረው
እኛ ፡ የምናመልከው ፡ ይህን ፡ ድንቅ ፡ ጌታ ፡ ነው

አዝክብር ፡ ለአንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ ክብር ፡ ለአንተ (፪x)
ክብር ፡ ለዘለዓለም ፡ ይገባሃል
አስደናቂ ፡ ጌታ ፡ ነህ ፡ አይተንሃል

የምድያንም ፡ ሰራዊት ፡ ቁጥሩ ፡ እጅግ ፡ ቢበዛም
ከእስራኤል ፡ ጭፍራ ፡ ጋር ፡ ባይመጣጠንም
ጌድዮን ፡ ግን ፡ በእምነት ፡ ወደ ፡ ሰልፉ ፡ ወጣ
ችቦን ፡ አነደደ ፡ መለከቱን ፡ ነፋ
ምድያም ፡ ተዋረደ ፡ ሸሸ ፡ ከእስራኤል ፡ ፊት
ለጌድዮን ፡ አምላክ ፡ ክብር ፡ ይሁንለት

አዝክብር ፡ ለአንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ ክብር ፡ ለአንተ (፪x)
ክብር ፡ ለዘለዓለም ፡ ይገባሃል
አስደናቂ ፡ ጌታ ፡ ነህ ፡ አይተንሃል

በአህያ ፡ መንጋጋ ፡ ሺ ፡ ሰው ፡ የገደለው
ኃይልን ፡ የተሞላው ፡ ሳምሶን ፡ የእግዚአብሔር ፡ ሰው
የአንበሳን ፡ ደቦል ፡ ደፍሮ ፡ የገጠመው
በእጁ ፡ ብርታት ፡ ሳይሆን ፡ በአምላኩ ፡ ጉልበት ፡ ነው
እኛ ፡ የምናመልከው ፡ ይህን ፡ ድንቅ ፡ ጌታ ፡ ነው

አዝክብር ፡ ለአንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ ክብር ፡ ለአንተ (፪x)
ክብር ፡ ለዘለዓለም ፡ ይገባሃል
አስደናቂ ፡ ጌታ ፡ ነህ ፡ አይተንሃል

አራት ፡ መቶ ፡ ሃምሳ ፡ የበዓል ፡ ነቢያት
ፉክክር ፡ ገጠሙ ፡ ቀርበው ፡ ከኤልያስ ፡ ፊት
በእሳት ፡ የሚመልስ ፡ እርሱ ፡ አምላክ ፡ ይሁን
በዚህ ፡ ሃሳብ ፡ ተስማምተው ፡ ጀመሩት ፡ ጩኸቱን
የኤልያስ ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ የመለሰው ፡ በእሳት
ለኤልያስ ፡ አምላክ ፡ ክብር ፡ ይሁንለት

አዝክብር ፡ ለአንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ ክብር ፡ ለአንተ (፪x)
ክብር ፡ ለዘለዓለም ፡ ይገባሃል
አስደናቂ ፡ ጌታ ፡ ነህ ፡ አይተንሃል

በእቶኑእሳት ፡ በሚወረወረው
በተራቡ ፡ አንበሶች ፡ ጉድጓድ ፡ ብንጣልም
ጠላት ፡ ደስ ፡ አይበልህ ፡ እኛስ ፡ አንጠፋም
የምናመልከው ፡ አምላክ ፡ የሚሳነው ፡ የለም
ደስ ፡ ደስ ፡ እያለን ፡ እልል ፡ እንበልለት
ለወደደን ፡ ጌታ ፡ ክብር ፡ ይሁንለት
ደስ ፡ ደስ ፡ እያለን ፡ እናሸብሽብለት
ላስደነቀን ፡ ጌታ ፡ ክብር ፡ ይሁንለት

አዝክብር ፡ ለአንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ ክብር ፡ ለአንተ (፪x)
ክብር ፡ ለዘለዓለም ፡ ይገባሃል
አስደናቂ ፡ ጌታ ፡ ነህ ፡ አይተንሃል