From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
አዝ፦ ክበር ፡ ክበር ፡ ክበር ፡ በሉት ፡ እርሱን (፪x)
ኢየሱስ ፡ ከፍ ፡ ሲል ፡ ያፈሳል ፡ መንፈሱን
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ብሎ ፡ ጠርቶው ተማፀኑ
ከተጠላት ፡ ጉያ ፡ ስር ፡ ወጥተው ፡ እንዲድኑ
በማዳኑ ፡ ጥላ ፡ ጋርዶ ፡ አበጃጅቷቸው
ለእግዚአብሔር ፡ ክብር ፡ ተናገር ፡ አላቸው
አዝ፦ ክበር ፡ ክበር ፡ ክበር ፡ በሉት ፡ እርሱን (፪x)
ኢየሱስ ፡ ከፍ ፡ ሲል ፡ ያፈሳል ፡ መንፈሱን
ሕያዋን ፡ ልጆቹ ፡ ክብርን ፡ እየሰጡ
በልዑል ማደሪያ ፡ ገብተው ፡ ተሸጐጡ
ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ብለው ፡ ሲዘምሩ
እየሰፋ ፡ ሄደ ፡ የወንጌል ፡ ድንበሩ
አዝ፦ ክበር ፡ ክበር ፡ ክበር ፡ በሉት ፡ እርሱን (፪x)
ኢየሱስ ፡ ከፍ ፡ ሲል ፡ ያፈሳል ፡ መንፈሱን
አባታቸው ፡ ከብሮአል ፡ በእነርሱ ፡ ምሥጋና
ሁላችሁ ፡ ተነሱ ፡ ይደርደር ፡ በገና
እስትንፋስ ፡ ያላችሁ ፡ ስገዱ ፡ አሜን ፡ በሉ
ኢየሱስ ፡ ሲነግስ ፡ የእኛ ፡ ነው ፡ ድሉ
አዝ፦ ክበር ፡ ክበር ፡ ክበር ፡ በሉት ፡ እርሱን (፪x)
ኢየሱስ ፡ ከፍ ፡ ሲል ፡ ያፈሳል ፡ መንፈሱን
እጆች ፡ ያጨብጭቡ ፡ ምላስም ፡ ይዘምር
የዳነ ፡ ህዝብ ፡ ሁሉ ፡ ይምጣ ፡ ለእርሱ ፡ ክብር
በደመቀ ፡ ዕልልታ ፡ አምላካችን ፡ ይንገሥ
ለማየት ፡ እንድንችል ፡ በረከቱን ፡ ሲያፈስ
አዝ፦ ክበር ፡ ክበር ፡ ክበር ፡ በሉት ፡ እርሱን (፪x)
ኢየሱስ ፡ ከፍ ፡ ሲል ፡ ያፈሳል ፡ መንፈሱን
|