ክብር ፡ ክብር (Keber Keber)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

የልጅነት ፡ ዘመን ፡ የፍንደቃ
ዳግም ፡ ሊሆንልን ፡ የዝማሬ
ጌታችን ፡ ተስፋህን ፡ አሰብክልን
ማስንቆ ፡ በገናን ፡ መለስክልን

አዝ፦ ሞገስ ፡ ሞገስ
ክብር ፡ ክብር
ላንተ ፡ ይሁን ፡ ጌታ
ክብር ፡ ክብር ፡ ሞገስ ፡ ሞገስ ፡ ላንት ፡ ይሁን

የውስጥ ፡ ሰቆቃችን ፡ ተለውጧል
ጌታ ፡ ሆይ ፡ በደጽ ፡ ተተክቷል
ዐይኖችህ ፡ ከሠማይ ፡ አዩንና
ለዝማሬ ፡ ቆምን ፡ እንደገና

አዝ፦ ሞገስ ፡ ሞገስ
ክብር ፡ ክብር
ላንተ ፡ ይሁን ፡ ጌታ
ክብር ፡ ክብር ፡ ሞገስ ፡ ሞገስ ፡ ላንት ፡ ይሁን

ከክትክታ ፡ በታች ፡ ተጋድመን
እንቅልፍ ፡ እንቅልፍ ፡ ብሎን ፡ ጠውልገን
አንተ ፡ አየህና ፡ አዘንክልን
ተራራ ፡ ለመውጣት ፡ አበቃን

አዝ፦ ሞገስ ፡ ሞገስ
ክብር ፡ ክብር
ላንተ ፡ ይሁን ፡ ጌታ
ክብር ፡ ክብር ፡ ሞገስ ፡ ሞገስ ፡ ላንት ፡ ይሁን

የጠላት ፡ ምኞቱ ፡ ተቆረጠ
ከእግራችን ፡ ስር ፡ ወድቆ ፡ ተረገጠ
በሰልፍ ፡ ለከበበን ፡ ታየህልን
ሞገስ ፡ መፈራትን ፡ አለበስከን

አዝ፦ ሞገስ ፡ ሞገስ
ክብር ፡ ክብር
ላንተ ፡ ይሁን ፡ ጌታ
ክብር ፡ ክብር ፡ ሞገስ ፡ ሞገስ ፡ ላንት ፡ ይሁን

ያለፈው ፡ ዘመናችን ፡ ታድሷል
ለምሥጋና ፡ ፍሬ ፡ ዛሬ ፡ በቅቷል
ተገፍቶ ፡ ተገፍቶ ፡ ሁሉን ፡ ላጣ
የጸድቅ ፡ የመጽናናት ፡ ዘመን ፡ መጣ

አዝ፦ ሞገስ ፡ ሞገስ
ክብር ፡ ክብር
ላንተ ፡ ይሁን ፡ ጌታ
ክብር ፡ ክብር ፡ ሞገስ ፡ ሞገስ ፡ ላንት ፡ ይሁን

የተስፋ ፡ አምላክ ፡ ነህ ፡ ማይታጣ
ለታላቁ ፡ ስምህ ፡ አበጃጀህ
ውበትህን ፡ ክብርን ፡ ጨመርክና
ዳግም ፡ ሰው ፡ አረከን ፡ እንደገና

አዝ፦ ሞገስ ፡ ሞገስ
ክብር ፡ ክብር
ላንተ ፡ ይሁን ፡ ጌታ
ክብር ፡ ክብር ፡ ሞገስ ፡ ሞገስ ፡ ላንት ፡ ይሁን