ክበር ፡ ጌታ ፡ ክበር (Keber Gieta Keber)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ክበር ፡ ጌታ ፡ ክበር
ክበር ፡ ኢየሱስ ፡ ክበር
ሞትን ፡ ባታሸንፍ ፡ ድል ፡ ሆነን ፡ ነበር
ዕልል! እንበል ፡ ዕልል! (፪x)
በዓለም ፡ ተሰራጭቷል ፡ የጌታችን ፡ ቃል

የምድር ፡ ወገኖች ፡ ዋይ ፡ ዋይ ፡ ይላሉ
የጌታ ፡ ወገኖች ፡ ደስታን ፡ ይለብሳሉ
የዘንባባ ፡ ቅጠል ፡ ይዘው ፡ ያጅባሉ

አዝ፦ ክበር ፡ ጌታ ፡ ክበር
ክበር ፡ ኢየሱስ ፡ ክበር
ሞትን ፡ ባታሸንፍ ፡ ድል ፡ ሆነን ፡ ነበር
ዕልል! እንበል ፡ ዕልል! (፪x)
በዓለም ፡ ተሰራጭቷል ፡ የጌታችን ፡ ቃል

ወንድሞች ፡ ተነሡ ፡ ቃሉን ፡ እንመስክር
እህቶች ፡ ተነሡ ፡ መዝሙር ፡ እንዘምር
በየቦታው ፡ ሁሉ ፡ ጌታ ፡ እንዲከብር

አዝ፦ ክበር ፡ ጌታ ፡ ክበር
ክበር ፡ ኢየሱስ ፡ ክበር
ሞትን ፡ ባታሸንፍ ፡ ድል ፡ ሆነን ፡ ነበር
ዕልል! እንበል ፡ ዕልል! (፪x)
በዓለም ፡ ተሰራጭቷል ፡ የጌታችን ፡ ቃል

የወንጌል ፡ መልዕክት ፡ ለሰዎች ፡ ንገሩ
ቃሉንም ፡ ይዛችሁ ፡ ሂዱ ፡ በያገሩ
ጌታን ፡ አክብራችሁ ፡ እናንተም ፡ ክበሩ

አዝ፦ ክበር ፡ ጌታ ፡ ክበር
ክበር ፡ ኢየሱስ ፡ ክበር
ሞትን ፡ ባታሸንፍ ፡ ድል ፡ ሆነን ፡ ነበር
ዕልል! እንበል ፡ ዕልል! (፪x)
በዓለም ፡ ተሰራጭቷል ፡ የጌታችን ፡ ቃል