ክበር ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታችን (Keber Eyesus Gietachen)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ክበር ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታችን ፡ ክበር ፡ በእኛ ፡ ላይ (፪x)
ውርደታችንን ፡ በክብር ፡ ለውተህ ፡ ልክ ፡ እንደቃልህ
ክብር ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታችን ፡ ክበርር ፡ በእኛ ፡ ላይ

ይውረድ ፡ ደመናህ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ይውረድ ፡ በእኛ ፡ ላይ (፪x)
ቤትህ ፡ በክብርህ ፡ ትሞላዋለህ ፡ ልክ ፡ እንደቃልህ
ይውረድ ፡ ደመናህ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ይውረድ ፡ በእኛ ፡ ላይ

ይንደድ ፡ እሳትህ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ እንደድ ፡ በእኛ ፡ ላይ (፪x)
መሷዕቱን ፡ ትብላ ፡ ወርዳ ፡ እሳትህ ፡ ልክ ፡ እንደቃልህ
እንደድ ፡ እሳትህ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ እንደድ ፡ በእኛ ፡ ላይ

አፍስስ ፡ ዘይትህን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ እፍስስ ፡ በእኛ ፡ ላይ (፪x)
ባዶ ፡ ማድጋን ፡ በዘይት ፡ ሞልተህ ፡ ልክ ፡ እንደቃልህ
አፍስስ ፡ ዘይትህን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ አፍስስ ፡ በእኛ ፡ ላይ