ከአቅምህ ፡ በላይ ፡ ሆኖ ፡ የሚከብድህ (Keaqemeh Belay Hono Yemikebdeh)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አዝ፦ ከአቅምህ ፡ በላይ ፡ ሆኖ ፡ የሚከብድህ
ለመፍታት ፡ ከቶ ፡ የሚያስቸግርህ
ምን ፡ ችግር ፡ አለ ፡ የሚያዳግትህ?
ሁሉን ፡ ቻይ ፡ የሆንክ ፡ ኤልሻዳይ ፡ አንተ ፡ ነህ

በሁለት ፡ ዓሣ ፡ በአምስት ፡ እንጀራ
አምስት ፡ ሺህ ፡ ያጠገብህ ፡ በበረሃ ፡ ሥፍራ
ዛሬም ፡ አይሳንህም ፡ ይህንን ፡ ልታደርግ
የደካከምነውን ፡ በቃል ፡ ልትባርክ

አዝ፦ ከአቅምህ ፡ በላይ ፡ ሆኖ ፡ የሚከብድህ
ለመፍታት ፡ ከቶ ፡ የሚያስቸግርህ
ምን ፡ ችግር ፡ አለ ፡ የሚያዳግትህ?
ሁሉን ፡ ቻይ ፡ የሆንክ ፡ ኤልሻዳይ ፡ አንተ ፡ ነህ

ለዕብራውያን ፡ መናህን ፡ ያዘነብህ
ዕውር ፡ ያበራህ ፡ ሽባን ፡ በእግሩ ፡ ያቆምህ
ዛሬም ፡ አይሳንህም ፡ ይህንን ፡ ልታደርግ
የዛለውን ፡ ጉልበት ፡ አድሰህ ፡ ልትልክ

አዝ፦ ከአቅምህ ፡ በላይ ፡ ሆኖ ፡ የሚከብድህ
ለመፍታት ፡ ከቶ ፡ የሚያስቸግርህ
ምን ፡ ችግር ፡ አለ ፡ የሚያዳግትህ?
ሁሉን ፡ ቻይ ፡ የሆንክ ፡ ኤልሻዳይ ፡ አንተ ፡ ነህ

የትኛው ፡ ደዌ ፡ ለፈውስ ፡ አስቸገረህ?
የትኛው ፡ ኃይል ፡ ተቋቁሞ ፡ ያዘህ?
የኃያላን ፡ ኃያል ፡ የነገሥታት ፡ ንጉሥ
ጠላትህን ፡ ረትተህ ፡ መንፈስህን ፡ አፍስስ

አዝ፦ ከአቅምህ ፡ በላይ ፡ ሆኖ ፡ የሚከብድህ
ለመፍታት ፡ ከቶ ፡ የሚያስቸግርህ
ምን ፡ ችግር ፡ አለ ፡ የሚያዳግትህ?
ሁሉን ፡ ቻይ ፡ የሆንክ ፡ ኤልሻዳይ ፡ አንተ ፡ ነህ

የሁሉም ፡ ዓይኖች ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ናቸው
ምስኪኖችህን ፡ መጥተህ ፡ ታደጋቸው
ነፋሳትን ፡ ሁሉ ፡ ማዕበሉንም ፡ አዛዥ
በመከራ ፡ ጊዜ ፡ የፃድቃን ፡ አጋዥ

አዝ፦ ከአቅምህ ፡ በላይ ፡ ሆኖ ፡ የሚከብድህ
ለመፍታት ፡ ከቶ ፡ የሚያስቸግርህ
ምን ፡ ችግር ፡ አለ ፡ የሚያዳግትህ?
ሁሉን ፡ ቻይ ፡ የሆንክ ፡ ኤልሻዳይ ፡ አንተ ፡ ነህ