ከአንቺ ፡ ላይ ፡ ይበራልና (Keanchi laay Yiberalina)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ከአንቺ ፡ ላይ ፡ ይበራልና
ፅዮን ፡ ተነሥተሽ ፡ አብሪ
አምላክ ፡ ከሰጠሽ ፡ ሥጦታ
ለዓለም ፡ አካፍይ
ጽጋግ ፡ ምድርን ፡ ሸፈነበት
ሰረጸ ፡ በሕዝብ ፡ ስሕተት
ምሪ ፡ በወንጌል ፡ ዕውቀት ።

ኢትዮጵያ ፡ ብርሃንሽ
እንዳይጨልም ፡ ወልውይ
ምቹ ፡ ጊዜ ፡ ገና ፡ ሳለሽ
ለሰላምሽ ፡ አስቢ
ባንቺ ፡ ዕውነት ፡ ቅናት ፡ ይልማ
የአምላክ ፡ መንግሥት ፡ ይስፋ
ፅድቅ ፡ በአገሩ ፡ ይግዛ ።

በተራራ ፡ የተሠራ
አገር ፡ ከሩቅ ፡ ይታያል
የዕውነትን ፡ ፍሬ ፡ እናፍራ
እንኑር ፡ በአምላክ ፡ ቃል
ጨው ፡ ለምድር ፡ ብርሃን ፡ ለዓለም
ሁነን ፡ ሕዝብን ፡ እንጥቀም
በትጋት ፡ አንለግም ።