ከክርስቶስ ፡ ጋር ፡ እስከኖራችሁ (KeKerestos Gar Eskenorachehu)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ከክርስቶስ ፡ ጋር ፡ እስከኖራችሁ
ሞታችሁ ፡ ለፅድቅ ፡ ሕያው ፡ ሆናችሁ
ሰማይና ፡ ምድር ፡ ቢደረማመስ
የፀጋው ፡ ኪዳን ፡ ለዘለዓለም ፡ አይፈርስ

በርቱ ፡ አትፍሩ ፡ ቁሙ ፡ በዕምነት
የጌታን ፡ ማዳን ፡ እዩ ፡ በድፍረት
ሁሉን ፡ ቻይ ፡ አለ ፡ ምን ፡ ጨነቃችሁ?
ባሕሩን ፡ ይከፍላል ፡ ትሄዳላችሁ

አዝ፦ እኛስ ፡ ተለይተናል ፤ በኢየሱስ ፡ ተመርጠናል
እግዚአብሔር ፡ ይመስገን ፡ ከሚሉት ፡ ሆነናል (፪x)

የእኛ ፡ አምላክ ፡ ምን ፡ ይሣነዋል?
ተራራን ፡ ንዶ ፡ ሜዳ ፡ ያደርገዋል
ዘምሩ ፡ ወደፊት ፡ ዘወትር ፡ ገስግሱ
ኃይላችሁ ፡ ይታደስ ፡ ጠጡት ፡ መንፈሱን

አዝ፦ እኛስ ፡ ተለይተናል ፤ በኢየሱስ ፡ ተመርጠናል
እግዚአብሔር ፡ ይመስገን ፡ ከሚሉት ፡ ሆነናል (፪x)

የሥጋን ፡ መሻት ፡ የሰይጣንን ፡ ጉሽም
ዘወትር ፡ ድል ፡ አድርጉት ፡ በኢየሱስ ፡ ስም
የክብር ፡ ተካፋይ ፡ እናንተ ፡ ሁሉ
ወንዱም ፡ ያጨብጭብ ፡ ሴቱም ፡ ዕልል ፡ በሉ

አዝ፦ እኛስ ፡ ተለይተናል ፤ በኢየሱስ ፡ ተመርጠናል
እግዚአብሔር ፡ ይመስገን ፡ ከሚሉት ፡ ሆነናል (፪x)