ከኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ጽድቅ ፡ በቀር (KeEyesus Kristos Tsdiq Beqer)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ከኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ጽድቅ ፡ በቀር
የምድንበት ፡ የለኝም
ግን ፡ በእርሱ ፡ አምኜ ፡ ልድፈር
የአምላክ ፡ ሕግ ፡ ሲከሰኝም
ለማመን ፡ ቢያስቸግርም
የኢየሱስ ፡ ቃል ፡ አይፋለስም

ሕይወት ፡ ሊሰጠኝ ፡ የሚችል
የኃጢአት ፡ ይቅርታ ፡ ነው
ከፍርድም ፡ የሚያስጠልል
ምሉ ፡ ይቅርታ ፡ ብቻ ፡ ነው
ይቅርታ ፡ ባይኖርልኝም
ተስፋና ፡ ሕይወት ፡ የለኝም

የምመካበት ፡ ጋሻዬ
የኃጢአት ፡ ይቅርታ ፡ ነው
በጭንቅም ፡ ሁሉ ፡ ደስታዬ
የኃጢአት ፡ ይቅርታ ፡ ነው
በኢየሱስ ፡ ደም ፡ ሥርየት ፡ ሳገኝ
እስከ ፡ ዘለዓለም ፡ ብፁዕ ፡ ነኝ

ኦ! ኢየሱስ ፡ ግሩም ፡ ይቅርታህን
በፀጋህ ፡ ሁሉ ፡ ቀን ፡ ስጠኝ
በልቤም ፡ ውስጥ ፡ ሰላምህን
ይቅርታህ ፡ ሁልጊዜ ፡ ይስጠኝ
በደምህ ፡ አምባ ፡ ውስጥ ፡ ስኖር
አልፈራም ፡ የጠላቴን ፡ ጦር