ከአምላክህ ፡ ፍርድ ፡ እንድትድን (KeAmlakh Fird Inditidin)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ከአምላክህ ፡ ፍርድ ፡ እንድትድን
በምን ፡ መሠረት ፡ ሠርተሃል?
በኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ተስፋህን
ስታደርግ ፡ ይበቃሃል
ቢሉኝ ፡ ምላሼ ፡ እንዲህ ፡ ነው
መሠረቴማ ፡ ጽኑ ፡ ነው
እርሱም ፡ የኢየሱስ ፡ መስቀል ፡ ነው
ደሙም ፡ ሕማማቱም

እስከ ፡ ዘለዓለም ፡ የማይወድቅ
አንድ ፡ ዓለት ፡ ይህ ፡ መሠረት ፡ ነው
የሕይወት ፡ ዘመኔም ፡ ሲያልቅ
ዕረፍቴ ፡ በእርሱ ፡ ነው
ከምድር ፡ ስሰናበትም
ልዘምር ፡ ስለ ፡ ኢየሱስ ፡ ደም
አሁንና ፡ ዘለዓለምም
ተስፋዬ ፡ እርሱ ፡ ነው