ከአምላካችን ፡ ማን ፡ ይበልጥ (KeAmlakachin Man Yibelt)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ከአምላካችን ፡ ማን ፡ ይበልጥ !
እንደ ፡ እርሱስ ፡ ማን ፡ ይሆናል!
ከሃሊ ፡ ኃይሉንም ፡ ሲገልጥ
እንዴት ፡ በጣም ፡ ይገርማል
በስድስት ፡ ቀን ፡ በኃይሉ ፡ ቃል
ምድራችንን ፡ አቁሟል
በእርሷም ፡ ያለውን ፡ ሁሉ

አምላክ ፡ የፈጠረውም ፡ ሁሉ
ግሩምና ፡ መልካም ፡ ነበር
እባቡ ፡ ግን ፡ በተንኮሉ
አጠፋው ፡ ሁሉን ፡ ነገር
በአባታችን ፡ ኃጢአት
ውርሳችን ፡ ሆኗል ፡ ጥፋት
በሁሉም ፡ ፍርድ ፡ ተጫነ

ግን ፡ አምላክ ፡ ሰው ፡ ሆኖልናል
በሕይወቱም ፣ በሞቱም
መድኃኒት ፡ ተገኝቶልናል
ከፍርዱ ፣ ከጥፋቱም
ፍዳችንን ፡ ተቀበለ
ዕዳችንንም ፡ ከፈለ
ተፈጸመ ፡ ሲል ፣ ሞተም

ይህንም ፡ የሚያምነው
በልቡም ፡ የሚቀበል
ይታጠባል ፡ ከበሽታው
በቅዱስ ፡ ደሙ ፡ ጠበል
ከክርስቶስ ፡ ጋራ ፡ ድኗል
ለነፍሱም ፡ ሕይወት ፡ ያገኛል
ከወንድሙ ፡ ከኢየሱስ

በዓብ ፣ በወልድ ፣ በመንፈስም
አገኘን ፡ ደኅንነት
ለሥሉስ ፡ አምላካችንም
ምሥጋና ፡ ይሁንለት
ከሞትና ፡ ከሰይጣን ፡ ኃይል
በኢየሱስ ፡ ፍፁም ፡ ድነናል
መድኃኒት ፡ ሆይ! ተመስገን