From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
ከአምላክ ፡ የራቅነውን ፡ ኃጥአን
ልጆቹ ፡ እንዲያደርግ
በንጹሕ ፡ ደሙ ፡ ገዛን
ያ ፡ ቅዱስ ፡ የአምላክ ፡ በግ
በልብህ ፡ ሥቃያችንን
ተሸክመህ ፡ ልባችንን
አዳንክ ፡ ኦ! ጌታ ፡ ኢየሱስ
ብርቱ ፡ የሚያስደንቅ
ሥቃይ ፡ ሲያስፈራራህ
መንፈስህም ፡ ሲጨነቅ
በጻርህ ፡ ለእኛ ፡ ራራህ
ጭንቃችንን ፡ ብታስብም
ሕማሙን ፡ አልተሰቀቅህም
ተመስገን ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ
እኛ ፡ እንድንባረክ
ተጫነ ፡ በአንተ ፡ መርገም
ጻርህ ፡ እንዴት ፡ ይተረክ
መስቀሉን ፡ ስትሸከም
የመቅሠፍት ፡ ጽዋ ፡ ጠጥተህ
ስለእኛ ፡ ነፍስህን ፡ ሰጥተህ
አዳንኸን ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ
የሱራፌልን ፡ ጭፍሮች
ሁሉ ፡ መጥራት ፡ ሲቻልህ
የአርያምም ፡ ኃይሎች
ሲታዘዙ ፡ ለቃልህ
በምድራችን ፡ ታስረህ
እስከሞት ፡ ድረሥም ፡ ታዝዘህ
ሞትህልን ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ
ግን ፡ ምሕረት ፡ ያላሳየህ
አምላክ ፡ ለእኔ ፡ ራራ
ልቤም ፡ ስለ ፡ ሥቃይህ
ይሆናል ፡ ከአንተ ፡ ጋራ
ልቤን ፡ እሰጥሃለሁኝ
ለአንተም ፡ እሆናለሁኝ
ለአንተ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ
|