From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
ካለህ ፡ የበለጠውን ፡ ስጥ
ወጣትነትህንም
ሁለመናህን ፡ አስረክብ
ለእውነት ፡ ወታደር ፡ ሁን
ኢየሱሥም ፡ ምሣሌህ ፡ ሆኖ
ራሱን ፡ ላምላክ ፡ አስገዛ
አንተም ፡ ለጌታ ፡ ታማኝ ፡ ሁን
የበለጠውን ፡ ስጠው
አዝ፦ ካለህ ፡ የበለጠውን ፡ ስጥ
ወጣትነትህንም
የአምላክን ፡ ጦር ፡ ዕቃ ፡ ልበስ
እውነትን ፡ ይዘህ ፡ ገስግስ
ካለህ ፡ የበለጠውን ፡ ስጥ
ልብህ ፡ ለጌታ ፡ ይሁን
በአገልግሎትህ ፡ ሁሉ ፡ ጌታህን ፡ አስቀድመው
አምላክ ፡ ወዶህ ፡ ልጁን ፡ ሰጠህ
ጽድቁንም ፡ አበራልህ
የአምላክን ፡ ፍቅር ፡ አስብ
የበለጠውን ፡ ስጠው
አዝ፦ ካለህ ፡ የበለጠውን ፡ ስጥ
ወጣትነትህንም
የአምላክን ፡ ጦር ፡ ዕቃ ፡ ልበስ
እውነትን ፡ ይዘህ ፡ ገስግስ
ካለህ ፡ የበለጠውን ፡ ስጥ
ወዶናል ፡ ይገባዋል
ለአንተ ፡ ሲል ፡ ሕይወቱን ፡ ሰዋ
የሰማይ ፡ ክብሩን ፡ ተወ
ሀፍረትህንም ፡ ወሰደ
ፅድቁንም ፡ ለአንተ ፡ ሰጠ
ውለታውን ፡ ሁሉ ፡ አስበው
የበለጠውንም ፡ ስጠው
አዝ፦ ካለህ ፡ የበለጠውን ፡ ስጥ
ወጣትነትህንም
የአምላክን ፡ ጦር ፡ ዕቃ ፡ ልበስ
እውነትን ፡ ይዘህ ፡ ገስግስ
|