ካልባረክኸኝ ፡ አልለቅህም (Kalbarekhegn Aleqehem)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ካልባረክኸኝ ፡ አልለቅህም (፪x)
ካልባረክኸኝ ፡ አልለቅህም (፪x)

ለብቻዬ ፡ ልቅር ፡ ፈቃድህ ፡ ከሆነ
ሌላው ፡ አይገደኝም ፡ ሕይወቴ ፡ ከዳነ
ሲሆን ፡ እስከ ፡ ንጋት ፡ ልታገልህና
ስደደኝ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ሕይወቴን ፡ ባርክና

አዝ፦ ካልባረክኸኝ ፡ አልለቅህም (፪x)
ካልባረክኸኝ ፡ አልለቅህም (፪x)

በመንበርከክ ፡ ብዛት ፡ በፀሎት ፡ ትግል
ፈቃድህ ፡ ከሆነ ፡ ጉልበቴ ፡ ይዛል
እያነከስኩ ፡ ይሁን ፡ እከተልሃለሁ
እጅህን ፡ ዘርጋልኝ ፡ በረከት ፡ እሻለሁ

አዝ፦ ካልባረክኸኝ ፡ አልለቅህም (፪x)
ካልባረክኸኝ ፡ አልለቅህም (፪x)

ሊነጋ ፡ ሲጀምር ፡ ሲቀላ
ወዴት ፡ እሄዳለሁ? ነፍሴ ፡ እንዲህ ፡ ዝላ
ሕይወቴን ፡ ብቻ ፡ ባርክ ፡ ሌላው ፡ አይገደኝም
ሥም ፡ እንዲሁ ፡ ቀሪ ፡ ነው ፡ ሥም ፡ አያድነኝም

አዝ፦ ካልባረክኸኝ ፡ አልለቅህም (፪x)
ካልባረክኸኝ ፡ አልለቅህም (፪x)

እንደ ፡ ያዕቆብ ፡ ዛሬ ፡ ጩኸቴን ፡ ስማና
ስደደኝ ፡ እባክህ ፡ ሕይወቴን ፡ ባርክና
ፈቃድህ ፡ ከሆነ ፡ ስሜንም ፡ ለውጠው
ሰው ፡ እንዳለ ፡ ሳይሆን ፡ አንተ ፡ እንደወደድከው

አዝ፦ ካልባረክኸኝ ፡ አልለቅህም (፪x)
ካልባረክኸኝ ፡ አልለቅህም (፪x)