የሩሣሌም ፡ ዕልል ፡ በይ (Jerusalem Elil Beyi)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

የሩሣሌም ፡ ዕልል ፡ በይ
የጽዮን ፡ ልጅም ፡ ዘምሪ
ንጉሥሽ ፡ ይመጣልና
በምድር ፡ ሁሉ ፡ ሊገዛ

ፀጋና ፡ ጽድቅን ፡ ሊሰጠን
ከአባቱ ፡ ተላከልን
ይሰጣልም ፡ ለሰው ፡ ሰላም
ከኃጢአት ፡ ሁሉ ፡ በማዳን

ምሥራች ፡ የነገረ ፡ መልዓክ
ተልኮልናል ፡ ከአምላክ
በእርሱ ፡ ያገኘነው ፡ ተስፋ
ይሰጠናል ፡ ታላቅ ፡ ደስታ

ስብሓት ፡ ለአምላክ ፡ በዓርያም
በዓለምም ፡ ይሁን ፡ ሰላም
ታላቅ ፡ ፀጋ ፡ ላመጣልን
በምሉ ፡ ልብ ፡ እናመስግን