እንሰብሰብ ፡ በዔድን ፡ አንድ ፡ ቀን (Insebseb BeEden Aind Qen)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

እንሰብሰብ ፡ በዔድን ፡ አንድ ፡ ቀን
ከዚህ ፡ ምድር ፡ ሥቃይ ፡ እንዳን
በእጃችን ፡ የሰሌን ፡ ዝንጣፊ ፡ ይዘን
እንቅረብ ፡ ወደ ፡ አምላክ ፡ ዙፋን
ወደ ፡ ላይ ፡ ስንደርስ
ወደ ፡ ላይ ፡ ስንደርስ
የዘለዓለም ፡ ብፅዕና ፡ ይሆነናል
ወደ ፡ ዔድን ፡ አንድ ፡ ቀን ፡ ስንደርስ ።

ስንደርስ ፡ ወደ ፡ ዔድን ፡ አንድ ፡ ቀን
ፃድቃን ፡ ሁሉ ፡ ይቀበሉናል
የሰማዕታት ፡ ጭፍራም ፡ ደስታችንን
ከኛ ፡ ጋራ ፡ ይካፈለዋል ።
ወደ ፡ ላይ ፡ ስንደርስ
ወደ ፡ ላይ ፡ ስንደርስ
የዘለዓለም ፡ ብፅዕና ፡ ይሆነናል
ወደ ፡ ዔድን ፡ አንድ ፡ ቀን ፡ ስንደርስ ።

ኢየሱሥም ፡ ወዲያ ፡ አድርሶን
እርሱ ፡ ራሱ ፡ ይቀበለናል
የሙሽራም ፡ ልብሣችንን ፡ አልብሶን
ከእርሱ ፡ ጋራ ፡ ያስቀምጠናል ።
ወደ ፡ ላይ ፡ ስንደርስ
ወደ ፡ ላይ ፡ ስንደርስ
የዘለዓለም ፡ ብፅዕና ፡ ይሆነናል
ወደ ፡ ዔድን ፡ አንድ ፡ ቀን ፡ ስንደርስ ።