እንደ ፡ እናት ፡ የሚመስል ፡ ማን ፡ አለ (Inde Enat Yemimesil Man Alle)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

እንደ ፡ እናት ፡ የሚመስል ፡ ማን ፡ አለ?
እንደ ፡ እናት ፡ ሁሉን ፡ የሚተካነ?
የለም ፡ በዓለም ፡ በፍቅር ፣ በርኅራኄ
እንደ ፡ እናቴ ፣ እንደ ፡ እናቴ ።

ከሕፃንነት ፡ ይዛ ፡ ሳትታክት
ተሸከመችን ፡ በትልቅ ፡ ትዕግሥት
የለም ፡ በዓለም ፡ በፍቅር ፣ በርኅራኄ
እንደ ፡ እናቴ ፣ እንደ ፡ እናቴ ።

ደስ ፡ ያሰኛታል ፡ በክብር ፡ ስንሸለም
በውርደታችን ፡ ከኛ ፡ አትርቅም
የለም ፡ በዓለም ፡ በፍቅር ፣ በርኅራኄ
እንደ ፡ እናቴ ፣ እንደ ፡ እናቴ ።

ደስታ ፡ ቢኖረን ፣ ጭንቀት ፡ ቢያሰለች
በማይክድ ፡ ዕምነት ፡ እናት ፡ ትረዳለች
የለም ፡ በዓለም ፡ በፍቅር ፣ በርኅራኄ
እንደ ፡ እናቴ ፣ እንደ ፡ እናቴ ።

የዋኅ ፡ እናት ፡ ያለ ፡ ደሞዝ ፡ ስለእኛ
ትደክማለች ፡ ሳይኖርት ፡ ምሥጋና
የለም ፡ በዓለም ፡ በፍቅር ፣ በርኅራኄ
እንደ ፡ እናቴ ፣ እንደ ፡ እናቴ ።

በዕምነት ፡ ጸንታ ፡ በሕይወት ፡ በሞትም
ሁሉ ፡ ቢጠሉን ፡ እናት ፡ አትክድም
የለም ፡ በዓለም ፡ በፍቅር ፣ በርኅራኄ
እንደ ፡ እናቴ ፣ እንደ ፡ እናቴ ።

ርኅሩኅ ፡ እናት ፡ በሞት ፡ ከኛ ፡ ስትነጠል
ሊጨልምብን ፡ ደስታችን ፡ ሊበጠስ
የለም ፡ በዓለም ፡ በፍቅር ፣ በርኅራኄ
እንደ ፡ እናቴ ፣ እንደ ፡ እናቴ ።

ከኛ ፡ ዘንድ ፡ ሳለች ፣ እናሳይ ፡ ክብረትን
ደስ ፡ እናሰኛት ፡ ጸጸት ፡ እንዳይመረን
የለም ፡ በዓለም ፡ በፍቅር ፣ በርኅራኄ
እንደ ፡ እናቴ ፣ እንደ ፡ እናቴ ።

ለአንቺ ፡ እናቴ ፡ ይገባል ፡ ምሥጋና
ዕድሜሽም ፡ ይርዘም ፣ ልብሽ ፡ ይምላ ፡ ደስታ
የለም ፡ በዓለም ፡ በፍቅር ፣ በርኅራኄ
እንደ ፡ እናቴ ፣ እንደ ፡ እናቴ ።