እንዳልተውህ ፡ እንዳልረሳህ ፡ ጌታ (Indaltewuh Indalresah Gieta)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አዝ ፣
እንዳልተውህ ፣ እንዳልረሳህ ፡ ጌታ
ጣርህን ፡ አስታውሰኝ ፣ በዚያች ፡ በጐልጐታ (፪X)

ምውት ፡ እንኳ ፡ ብሆን ፣ ለመንቃት ፡ የማልችል
የቃልህን ፡ ምሥጢር ፡ ጌታ ፡ ሆይ! ልቀበል
በድካሜ ፡ ብዛት ፣ ኢየሱስ ፡ ሆይ! እንዳልወድቅ
የመስቀልህን ፡ ምሥጢር ፡ ጠለቅ ፡ ብዬ ፡ ልወቅ

አዝ ፣
እንዳልተውህ ፣ እንዳልረሳህ ፡ ጌታ
ጣርህን ፡ አስታውሰኝ ፣ በዚያች ፡ በጐልጐታ (፪X)

ፀጋህ ፡ እንደማይለየኝ ፣ አምላኬ ፡ ሆይ! ባውቅም
መውደቅም ፡ ስለአለ ፡ በመቆሜ ፡ አላምንም
ስለዚህ ፡ ጌታ ፡ ሆይ! በፀጋህ ፡ አቁመኝ
ብቻዬን ፡ የማልችል ፡ እኔ ፡ ደካማ ፡ ነኝ

አዝ ፣
እንዳልተውህ ፣ እንዳልረሳህ ፡ ጌታ
ጣርህን ፡ አስታውሰኝ ፣ በዚያች ፡ በጐልጐታ (፪X)

በስደትም ፡ ቢሆን ፡ ለስምህ ፡ ለመሞት
ኃይልን ፡ ብትሰጠኝም ፡ ከመንፈስህ ፡ ሙልዓት
ይህን ፡ እረስቼ ፡ እንዳልመለስ
እንደ ፡ ሶምሶን ፡ ኃይልን ፡ በላዬ ፡ ላይ ፡ አፍስስ

አዝ ፣
እንዳልተውህ ፣ እንዳልረሳህ ፡ ጌታ
ጣርህን ፡ አስታውሰኝ ፣ በዚያች ፡ በጐልጐታ (፪X)