ሁሉንም ፡ እንደየአቅሙ (Hulunem Endeyeaqemu)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

በፍቅር ፡ እጆችህ ፡ ይዘህ
በቤትህ ፡ ታኖረዋለህ
መጽናናትን ፡ ሰላምን ፡ ሞልተህ
ለመንጋህ ፡ የምትራራ
መልካም ፡ እረኛ ፡ አንተ ፡ ነህ
በፍፁም ፡ የሚመስልህ ፡ የለም
አንተ ፡ ከሁሉም ፡ በላይ ፡ ነህ

አዝ፦ ተመሥገን ፡ ከፍ ፡ በል ፡ ጌታ
ምሥጋና ፡ ይብዛ ፡ ዘለዓለም
ለህዝብህ ፡ መልካም ፡ እረኛ
እንዳንተ ፡ ያለ ፡ አምላክ ፡ የለም

ለአገልግሎትህ ፡ ሾምከኝ
ታማኞች ፡ አድርገህ ፡ ቆጠርከን
እጅግ ፡ ደካሞች ፡ ብንሆንም
በፀጋህ ፡ ሁሉን ፡ አስቻልከን
በአዲስ ፡ ራዕይ ፡ መራሐን
በሕያው ፡ ቃልህ ፡ ደገፍከን
በወንዞች ፡ ዳርቻ ፡ ተክለህ
በቤትህ ፡ አለመለምከን

አዝ፦ ተመሥገን ፡ ከፍ ፡ በል ፡ ጌታ
ምሥጋና ፡ ይብዛ ፡ ዘለዓለም
ለህዝብህ ፡ መልካም ፡ እረኛ
እንዳንተ ፡ ያለ ፡ አምላክ ፡ የለም

ዳርቻችን ፡ ሁሉ ፡ ሰፍቶ
ቁጥራችንም ፡ እጅግ ፡ በዝቶ
ልባችን ፡ ደስታ ፡ ተሞላ
ስናየው ፡ መቅደሽ ፡ ሞልቶ
መጽናናት ፡ ሰላም ፡ በዛልን
ግርማ ፡ ሞገስን ፡ ሰጠኸን
ተመስገን ፡ ክበር ፡ ጌታችን
ሌላማ ፡ ምን ፡ እንላለን

አዝ፦ ተመሥገን ፡ ከፍ ፡ በል ፡ ጌታ
ምሥጋና ፡ ይብዛ ፡ ዘለዓለም
ለህዝብህ ፡ መልካም ፡ እረኛ
እንዳንተ ፡ ያለ ፡ አምላክ ፡ የለም

ፊት ፡ ቀድመህ ፡ እየመራኸን
ከኋላም ፡ ተከትለኸን
ከጥፋት ፡ ሁሉ ፡ ጋረድከን
በእሳት ፡ አምድህ ፡ አጠርከን
በስምህ ፡ ድልን ፡ አገኘን
ታላቅነትህን ፡ አየን
ተመስገን ፡ ስምህ ፡ ይባረክ
ለክብርህ ፡ እንዘምራለን

አዝ፦ ተመሥገን ፡ ከፍ ፡ በል ፡ ጌታ
ምሥጋና ፡ ይብዛ ፡ ዘለዓለም
ለህዝብህ ፡ መልካም ፡ እረኛ
እንዳንተ ፡ ያለ ፡ አምላክ ፡ የለም