ሁሉን ፡ አየነው ፡ ሁሉን ፡ አለፍን (Hulun Ayenew Hulun Alefn)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አዝ ፣
ሁሉን ፡ አየነው ፡ ሁሉን ፡ አለፍን
ጌታን ፡ መረጥን
በእርሱ ፡ ላይ ፡ ቆምን (፪X)

በሚያስፈራው ፡ ዘመን ፡ ዙሪያው ፡ በተዘጋ
ቆመን ፡ ከእርሱ ፡ ጋር
እኛም ፡ ተቆጠርን ፡ ብለን ፡ ነበር ፡ ቀድሞ
ኢየሱስ ፡ ዋጀን ፡ ደግሞ ፡ (፬X)

አዝ ፣
ሁሉን ፡ አየነው ፡ ሁሉን ፡ አለፍን
ጌታን ፡ መረጥን
በእርሱ ፡ ላይ ፡ ቆምን (፪X)

ዓይናችን ፡ ማየቱን ፡ አቁሞ ፡ ነበረ
ፍፁም ፡ ታወረ
እግራችን ፡ መሄዱን ፡ ተሳሰረ ፡ አበቃ
በፈተና ፡ ሲቃ

አዝ ፣
ሁሉን ፡ አየነው ፡ ሁሉን ፡ አለፍን
ጌታን ፡ መረጥን
በእርሱ ፡ ላይ ፡ ቆምን (፪X)

ለካስ ፡ ይታለፋል ፡ ያ ፡ ሁሉ ፡ በረሃ
በሌለበት ፡ ውሃ
እግዚአብሔር ፡ እርካታ ፡ ይሆናል ፡ ለድሃ
በሌለበት ፡ ውኃ (፬X)

አዝ ፣
ሁሉን ፡ አየነው ፡ ሁሉን ፡ አለፍን
ጌታን ፡ መረጥን
በእርሱ ፡ ላይ ፡ ቆምን (፪X)

ዮርዳኖስ ፡ ሲሞላ ፣ ልብ ፡ ስንጥቅ ፡ ሲል!
ኢየሱስ ፡ ያግዛል
ባሕሩን ፡ ሰንጥቆ ፡ ሰላምን ፡ መሥርቶ
ያሻግራል ፡ ማዶ (፬X)

አዝ ፣
ሁሉን ፡ አየነው ፡ ሁሉን ፡ አለፍን
ጌታን ፡ መረጥን
በእርሱ ፡ ላይ ፡ ቆምን (፪X)