From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
፩ ቆሮንጦስ ፱ ፡ ፳፱
ሁሉም ፡ ሩጠው ፡ አክሊል ፡ አንድ ፡ ያገኛል
ወንድሜ ፡ እንድታገኘው ፡ ጣር
ፊት ፡ የገቡት ፡ ወደ ፡ አምላክ ፡ ፀዳል
ይመለከታሉ ፡ የአንተን ፡ ጻር
ስትሮጥም ፡ ዓይንህ ፡ አይገላመጥ
የከንቱን ፡ ደስታ ፡ አትመኝ
መንፈስ ፡ ቅዱሥም ፡ የሚለውን ፡ አድምጥ
ቅዱስ ፡ አክሊሉን ፡ እንድታገኝ
የሚጠፋውን ፡ አክሊል ፡ ለማግኘት
የሚመኝ ፡ በጣም ፡ ይጋደላል
አንተም ፡ ለዘለዓለም ፡ ደህንነት
ዓለምን ፡ መካድ ፡ ይገባሃል
የዚህ ፡ ዓለም ፡ ጥቅም ፡ ምን ፡ ይረባል
እንደ ፡ ጢስ ፡ ይሸሻል ፡ ደስታው
ኢየሱስ ፡ የሚሰጠው ፡ ግን ፡ ይቆያል
በእርሱ ፡ የያምን ፡ ብፁዕ ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ ለአንተ ፡ መስቀሉን ፡ ሲሸከም
ቅዱስ ፡ አክሊሉን ፡ ዋጅቶልሃል
በእርሱ ፡ የእሾህ ፡ ዘውድ ፡ ስለተጫነም
የብፅዕና ፡ ዘውድ ፡ ይቆይሃል
የሰማይን ፡ ርስት ፡ እንዳታባክን
እንዳታጣ ፡ ቅዱስ ፡ አክሊሉን
በመድኃኒታችን ፡ ግን ፡ ስታምን
እስከ ፡ ሞት ፡ ድረስ ፡ የፀናህ ፡ ሁን
|