ሕይወቴን ፡ ውሰድ (Hiwotien Wesed)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ሕይወቴን ፡ ውሰድና
የተቀደሰ ፡ ይሁን
እጆቼን ፡ ውሰድና
በአንተ ፡ ይታዘዙልኝ
በአንተ ፡ ይታዘዙልኝ

እግሬንም ፡ አንተው ፡ እዘዝ
አንተኑ ፡ ያገልግልህ
ድምጼንም ፡ እንደዚሁ
አንተው ፡ ተጠቀምበት
አንተው ፡ ተጠቀምበት

ሁለመናዬን ፡ ውሰድ
ፍፁም ፡ ለአንተ ፡ እንድሆን
የራሴም ፡ አይደለሁም
የአንተ ፡ የአምላኬ ፡ ነኝ
የአንተ ፡ የአምላኬ ፡ ነኝ