ሕይወቴን ፡ ለወጥኩልህ (Hiwotien Lewetkuleh)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ሕይወቴን ፡ ለወጥኩልህ ፡ ልገዛ ፡ ነፍስህን
ሰማይን ፡ ልከፍትልህ ፡ ልሰጥህ ፡ ርስትህን
ትድን ፡ ዘንድ ፡ ደሜ ፡ ፈስዋል
ምን ፡ መልሰህልኛል

ስላንተ ፡ ብፅዕና ፡ እኔ ፡ ተሰቃየሁ
ስላንተም ፡ ብልጥግና ፡ እኔ ፡ ደኸየሁ
ስላንተ ፡ ሁሉንም ፡ ትቼ
ምን ፡ ሆነ ፡ ደመወዜ

ከኃጢአት ፡ ከሞትም ፡ ላድንህ ፡ መጣሁ
በልብህ ፡ ውስጥ ፡ ልኖርም ፡ ድጅህን ፡ መታሁ
ስጠኝ ፡ ኦ ፡ ልጄ ፡ ምኞቴን
ልብህን ፡ ደመወዜን