ሕዝቦች ፡ ሆይ ፡ ደስ ፡ ይበላችሁ (Hezboch Hoy Des Yebelachehu)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ሕዝቦች ፡ ሆይ ፡ ደስ ፡ ይበላችሁ
አምላክን ፡ አመስግኑ
የቆማችሁ ፡ በኪዳኑ
በአንድነት ፡ ቅረቡ
ቅረቡ ፡ በዕልልታ
ዘምሩ ፡ ለቸር ፡ ጌታ (፪x)

እርሱ ፡ ነው ፡ የፈጠረነ
ልጆቹን ፡ የጠራነ
የጠፉትንም ፡ ያዳነ
እስካሁን ፡ ያቆመነ
እርሱ ፡ በሰማይ ፡ ደስታ
አደራጀልን ፡ ስፍራ (፪x)

ዘምሩለት ፡ በበሮቹ
ወድሱት ፡ በመቅደሱ
ከአገር ፡ ሁሉ ፡ ተከማቹ
ለአባታችን ፡ ስገዱ
ርኅሩኅ ፡ ሆኖ ፡ ያፀናል
እስከ ፡ ሞት ፡ ይመራናል (፪x)