ሕዝቤ ፡ ሆይ ፡ ና (Hezbie Hoy Na)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ሕዝቤ ፡ ሆይ ፡ ና ፡ ይላል ፡ እግዚአብሔር
ወደ ፡ ቤትህ ፡ ግባ ፡ ከግርግር
ጥላ ፡ ልሁንልህ ፡ ከጠራራው ፡ ፀሐይ
ከጥፋት ፡ ውሽንፍር

ልጆችን ፡ ወለድሁ ፡ አሳደኩም
እነርሱ ፡ ግን ፡ እኔን ፡ አላወቁም
በሬ ፡ እንኳን ፡ የገዥውን ፡ ጋጣ ፡ አወቀ
ሕዝቤ ፡ ግን ፡ ከአምላኩ ፡ ለምን ፡ ራቀ?

አዝ፦ ሕዝቤ ፡ ሆይ ፡ ና ፡ ይላል ፡ እግዚአብሔር
ወደ ፡ ቤትህ ፡ ግባ ፡ ከግርግር
ጥላ ፡ ልሁንልህ ፡ ከጠራራው ፡ ፀሐይ
ከጥፋት ፡ ውሽንፍር

ጉድጓድ ፡ በብዛት ፡ መቆፈሩ
በውኃ እጦት ፡ መባረሩ
አይበቃችሁም ፡ ወይ ፡ መባከኑ
የሕይወት ፡ ምንጭ ፡ ነኝ ፡ ወደ ፡ እኔ ፡ ኑ

አዝ፦ ሕዝቤ ፡ ሆይ ፡ ና ፡ ይላል ፡ እግዚአብሔር
ወደ ፡ ቤትህ ፡ ግባ ፡ ከግርግር
ጥላ ፡ ልሁንልህ ፡ ከጠራራው ፡ ፀሐይ
ከጥፋት ፡ ውሽንፍር

ለሆድህ ፡ አትገዛ ፡ እንደላሞች
በስብሰህ ፡ አትቀርም ፡ እንደ ፡ ዛፎች
አስትንፋስ ፡ አለብህ ፡ አንተ ፡ የእኔ ፡ ነህ
በመጨረሻው ፡ ቀን ፡ ትነሳለህ

አዝ፦ ሕዝቤ ፡ ሆይ ፡ ና ፡ ይላል ፡ እግዚአብሔር
ወደ ፡ ቤትህ ፡ ግባ ፡ ከግርግር
ጥላ ፡ ልሁንልህ ፡ ከጠራራው ፡ ፀሐይ
ከጥፋት ፡ ውሽንፍር

በትናንቱ ፡ ድምጽ ፡ አጣራለሁ
ዛሬም ፡ ቸርነቱን ፡ አሳያለሁ
የሚጸጸት ፡ ካለ ፡ እምራለሁ
ሕዝቤ ፡ ሲጠፋብኝ ፡ እቀናለሁ

አዝ፦ ሕዝቤ ፡ ሆይ ፡ ና ፡ ይላል ፡ እግዚአብሔር
ወደ ፡ ቤትህ ፡ ግባ ፡ ከግርግር
ጥላ ፡ ልሁንልህ ፡ ከጠራራው ፡ ፀሐይ
ከጥፋት ፡ ውሽንፍር