ህፃን ፡ ተወለደ ፡ በዚህ ፡ ሌት (Hetsan Tewelede Bezih Liet)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ህፃን ፡ ተወለደ ፡ በዚህ ፡ ሌት
ያን ፡ ቅዱስ ፡ ህፃኑን ፡ እናክብር
በእርሱ ፡ ላይ ፡ አለ ፡ የአብ ፡ ሥምረት
በእኛም ፡ ትምሕርቱ ፡ ይዳብር
ይህ ፡ ህፃን ፡ ባይወለድ
በጠፋን ፡ ሁላችንም
አሁን ፡ ግን ፡ ሕይወት ፡ አለን
ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ተመስገን
በአንተ ፡ ተስፋ ፡ አግኝተን
ለአንተ ፡ እንሰግዳለን

እረኞች ፡ መንጋቸውን ፡ ሲጠብቁ
በሌሊት ፡ በሜዳ ፡ ሲቆዩ
በሰሙት ፡ ነገር ፡ ተደነቁ
የአምላክን ፡ ክብርም ፡ አዩ
መልዓክ ፡ እንዲህ ፡ ሲል ፡ ዘመረ
መድህን ፡ ዛሬ ፡ ተወለደ
እርሱም ፡ በዳዊት ፡ አገር
ጌታችን ፡ ነው ፡ በእርሱም ፡ ሥልጣን
የአምላክ ፡ የግርማው ፡ ብርሃን
ተገለጠ ፡ በምድር

መላዕክትም ፡ ደግሞ ፡ በታላቅ ፡ ቃል
አምላክን ፡ ይወድሱ ፡ ጀመር
በቅዱሳን ፡ በሰማይ ፡ ፀዳል
ዘለዓለሙ ፡ እንደሚዘመር
ለአምላክ ፡ ውዳሴ ፡ ይሁን
በምድርም ፡ ሰላም ፡ ይሁን
በጐም ፡ ፈቃድ ፡ አይተወን
ኦ ፡ ርኅሩኅ ፡ አምላክ ፡ ተመስገን
ከልጅህ ፡ ጋር ፡ ከሰጠኸን
ከፀጋህ ፡ አትለየን