ሕፃን ፡ ተወልዷል ፡ በቤተሌሔም (Hetsan Teweldual Bebethlehem)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ሕፃን ፡ ተወልዷል ፡ በቤተልሔም ፤ ቤተልሔም
ደስ ፡ ይበልሽ ፡ ኢየሩሳሌም
ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ

እናቱ ፡ ማርያም ፡ ንጽሕይት ፡ ድንግል ፡ ናት ፤ ድንግል ፡ ናት
አባቱም ፡ አብ ፡ በሰማያት
ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ

በበረት ፡ ውስጥ ፡ ሕፃኑን ፡ አኖሩ ፤ አኖሩ
መላእክትም ፡ ለእርሱ ፡ ዘመሩ
ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ

ሰብዓ ፡ ሰገልም ፡ መጥተው ፡ ሰዉለት ፤ ሰዉለት
ወርቅና ፡ ዕጣን ፡ ከርቤም ፡ ሰጡት
ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ

መድሃኒት ፡ ያ ፡ ሕፃን ፡ ሁኖልናል ፡ ሆኗል
ጭንቃችንም ፡ ተሽሯል
ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ

የአምላክ ፡ ልጅ ፡ በፍቅሩ ፡ መጣልን ፤ መጣልን
በእርሱም ፡ ደስ ፡ ይበለን
ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ

አወረደልን ፡ ከአብ ፡ ሥምረቱን ፤ ሥምረቱን
በደስታ ፡ እናያለን ፡ ፊቱን
ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ

መላእክት ፡ ስለእርሱ ፡ እንደዘመሩ ፡ ዘምሩ
እናንተም ፡ ምሥጋናውን ፡ አውሩ
ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ

ለቸሩ ፡ አምላክ ፡ ይሁን ፡ ክብር ፤ ክብር
ሰላምም ፡ በእኛ ፡ በምድር
ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ