ሕፃን ፡ ተወልዶልናል (Hetsan Teweldolenal)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ሕፃን ፡ ተወልዶልናል ፡ ልጅም ፡ ተሰጠን
ከአምላክ ፡ በደም ፡ በሥጋም ፡ ተገናኘን
ከሰው ፡ ዘር ፡ ከሴቶቹ ፡ እናቱን ፡ መርጦ
በውርደት ፡ ተወለደ ፡ ፍቅሩን ፡ ገልጦ

ፈጣሪ ፡ ከፍጥረቱ ፡ ጋራ ፡ ተዛምዶ
ከኃጢአተኞችም ፡ ቅዱስ ፡ ተጣምዶ
አብ ፡ ወልድን ፡ ከላከ ፡ ሊሆን ፡ ዘመዳችን
ምህረቱን ፡ ላሳየን ፡ ይረግ ፡ ምሥጋናችን

በውድቀቱ ፡ አዳም ፡ ላወረሰን ፡ ሁሉ
መድኃኒት ፡ ተገኘ ፡ በበረት ፡ በጐሉ
ስርየት ፡ ልናገኝ ፡ ስለ ፡ ኃጢአታችን
የዓለም ፡ ፈራጅ ፡ ሆኗል ፡ ወንድማችን

የታሰሩትን ፡ ሁሉ ፡ አወጣ ፡ አርነት
ከሞት ፡ ከቅጣትም ፡ አበጀ ፡ ነጻነት
ጠላቶቹን ፡ ሁሉ ፡ በኃይል ፡ ድል ፡ ይነሳል
ለኃጢአተኞች ፡ ይቅርታን ፡ ይለግሳል

በበረት ፡ በጐሉ ፡ የተኛ ፡ ሕጻኑ
ሰው ፡ እርሱን ፡ ሊወድስ ፡ አይበቃውም ፡ ልሳኑ
በውርደቱ ፡ ክብሩ ፡ ተደብቆ ፡ ባይታይም
መዳንን ፡ ብፅዕናን ፡ ግን ፡ ዋጀ ፡ ለዓለም

ይህንን ፡ ብፅዕና ፡ በቃሉ ፡ ይሰጣል
በቃሉም ፡ የፀጋ ፡ ፈቃዱን ፡ ይገልጣል
ስጦታውንም ፡ ለግሶ ፡ ለሁሉ ፡ ሲሰጠው
ልባችንን ፡ አጽንተን ፡ ቸል ፡ አንበለው

ይልቅ ፡ ልንቀበለው ፡ እንስገድለት
እንዲህም ፡ ስንል ፡ እንዘምር ፡ በእምነት
በምድር ፡ ተወልደህ ፡ መዳን ፡ የሆንህልን
ኦ ፡ ቸር ፡ ወንድማችን ፡ ኦ ፡ አምላክ ፡ ተመስገን