ሕግ ፡ ፈረደብን (Heg Feredeben)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ሕግ ፡ ፈረደብን ፡ ምህረት ፡ እንለምን
ፀጋህን ፡ ለግስ ፡ ፍርድን ፡ ስንለብስ
ትል ፡ ነን ፡ እኛ ፡ የሚበን ፡ ትቢያ
አላፊ ፡ ጥላ

ጠገግ ፡ ከብዶን ፡ ኃጢአት ፡ ወረሰን
ምኞትም ፡ ነዳን ፡ ፈተና ፡ አሳተን
ደካሞች ፡ ነን ፡ አትቅሰፈን
ተቀበለን

ስለ ፡ ስቃዩ ፡ ስለ ፡ እሾህ ፡ ዘውዱ
ኢየሱስ ፡ የጫነ ፡ ሊያስታርቀን
አምላክ ፡ ራራልን ፡ አትፍረድብን
አባት ፡ ሁንልን

በቅዱስ ፡ ደሙ ፡ የወጣ ፡ ከጐኑ
እንድናለን ፡ ይጠጋል ፡ ቁስላችን
የዋህ ፡ እረኛ ፡ የከዳውን ፡ ጠራ
ና ፡ ወደ ፡ መንጋ

አምላክ ፡ እርዳን ፡ በኢየሱስ ፡ ማረን
ሲማልደልን ፡ ፀሎቱን ፡ ስማልልን
እንጮሃለን ፡ ደምስስ ፡ ኃጢአታችንን
አምላክ ፡ እይልን