ሀዘንተኛን ፡ ያፅናናው (Hazentegnan Yatsnanaw)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ሀዘንተኛን ፡ ያፅናናው
የመድኃኒታችን ፡ ሥም
ያንን ፡ ቅዱስ ፡ ሥም ፡ የጠራው
ይረዳል ፡ ይድናልም

አዝ፦ ቅዱስ ፡ ሥም ፡ ብፁዕ ፡ ሥም
የዘለዓለም ፡ ተስፋ ፡ ነው (፪x)

ብርቱ ፡ ጋሻም ፡ ይሁንለት
ኃጢአት ፡ ሲፈትነው
ልመናውም ፡ ይፈፀምለት
ከኢየሱስ ፡ የለመነው

አዝ፦ ቅዱስ ፡ ሥም ፡ ብፁዕ ፡ ሥም
የዘለዓለም ፡ ተስፋ ፡ ነው (፪x)

ያ ፡ ክቡር ፡ የኢየሱስ ፡ ሥምም
ብፅዕናን ፡ ይሰጠናል
ሕይወት ፡ ደስታም ፡ ሰላምም
ከዚህ ፡ ሥም ፡ አግኝተናል

አዝ፦ ቅዱስ ፡ ሥም ፡ ብፁዕ ፡ ሥም
የዘለዓለም ፡ ተስፋ ፡ ነው (፪x)

ወደ ፡ ሰማያዊ ፡ አገር
አድኖ ፡ ሲያደርሰን
ያንን ፡ ሥም ፡ ለአምላክ ፡ ክብር
እንዘምር ፡ አክብረን

አዝ፦ ቅዱስ ፡ ሥም ፡ ብፁዕ ፡ ሥም
የዘለዓለም ፡ ተስፋ ፡ ነው (፪x)