ኃይል ፡ ነው ፡ ኃይላችን ፡ ነው (Hayl New Haylachen New)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ኃይል ፡ ነው ፡ ኃይላችን ፡ ነው
ኃይላችን ፡ ነው ፡ ኃይላችን ፡ ነው

ይኸ ፡ የመዳን ፡ ወንጌል ፡ ለዓለም ፡ ሞኝነት ፡ ነው
ይኸ ፡ የመስቀሉ ፡ ቃል ፡ ለዓለም ፡ ሞኝነት ፡ ነው
ለምናምነው ፡ ለእኛ ፡ ግን ፡ የእግዚአብሔር ፡ ኃይል ፡ ነው
ለምናምነው ፡ ለእኛ ፡ ግን ፡ የእግዚአብሔር ፡ ኃይል ፡ ነው

አዝ፦ ኃይል ፡ ነው ፡ ኃይላችን ፡ ነው
ኃይላችን ፡ ነው ፡ ኃይላችን ፡ ነው

ቀንበራችንን ፡ ሰብሮ ፡ ከእሥራት ፡ ፈቶናል
ጌታ ፡ በወንጌሉ ፡ ነፃ ፡ አውጥቶናል
ለዓለም ፡ ሞኝ ፡ የሆነው ፡ የጌታችን ፡ ሞቱ
ለእኛ ፡ ጠቅሞናል ፡ ክብር ፡ ለብርታቱ

አዝ፦ ኃይል ፡ ነው ፡ ኃይላችን ፡ ነው
ኃይላችን ፡ ነው ፡ ኃይላችን ፡ ነው

ፍፁም ፡ አይከፋንም ፡ ዓለም ፡ ቢተፋብን
እኛ ፡ እናውቀዋለን ፡ ጉዳት ፡ ጥቅማችንን
አውቀናል ፡ እያሉ ፡ ሞት ፡ ሲነዳቸው
እንፀልያለን ፡ ኢየሱስ ፡ ያድናቸው

አዝ፦ ኃይል ፡ ነው ፡ ኃይላችን ፡ ነው
ኃይላችን ፡ ነው ፡ ኃይላችን ፡ ነው

በወንጌሉ ፡ ብርሃን ፡ ኢየሱስን ፡ አይተናል
በጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሞት ፡ ከእግዚአብሔር ፡ ታርቀናል
በመዳናችን ፡ ቀን ፡ የጠራን ፡ እርሱ ፡ ነው
በወንጌሉ ፡ አናፍርም ፡ ለእኛ ፡ ኃይል ፡ ነው

አዝ፦ ኃይል ፡ ነው ፡ ኃይላችን ፡ ነው
ኃይላችን ፡ ነው ፡ ኃይላችን ፡ ነው