ኃጢአተኞችን ፡ እንዲያድን (Hatiyategnochen Endiyaden)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ኃጢአተኞችን ፡ እንዲያድን
መድኃኒታችን ፡ ተልኳል
ያን ፡ ጥልቅ ፡ የአምላክ ፡ ምሥጢር ፡ ለማመን
ያን ፡ ቃል ፡ መቀበል ፡ ይገባናል

አሁን ፡ በዓለም ፡ ወንጌል ፡ ይሰፋል
መስፋቱን ፡ ማን ፡ ይከለክላል?
ያ ፡ ሰማይዊ ፡ እሣት ፡ ይነዳል
ብርሃን ፡ በሌሊት ፡ ይሰጠናል

በኢየሱስ ፡ ኃይል ፡ ዕውራን ፡ ያያሉ
የዲዳ ፡ አፍም ፡ ይናገራል
በደስታ ፡ ሽባዎችም ፡ ይዘላሉ
ከሞት ፡ አልዓዛር ፡ ይመለሳል

በዚህ ፡ የወደቀውን ፡ ደረቅ ፡ ቅልጥም
ኦ! ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ተመልከተው
የሕይወት ፡ መንፈስ ፡ የሞተውን ፡ አጥንት
ሥጋን ፡ ጅማትንም ፡ ያልብሰው

ሰማይን ፡ ቀደህ ፡ በወረድህልን
ዓለት ፡ ይሰበር ፡ ድንጋይ ፡ ይቅለጥ
በበረሃ ፡ መናን ፡ አውርድልን
የመስቀልህንም ፡ ኃይል ፡ ግለጥ

በእግርህ ፡ ታች ፡ አሕዛብ ፡ ይስገዱ
የአልጋህ ፡ ግርማ ፡ በዚህ ፡ ይምላ
ከፀጋ ፡ ምንጭ ፡ ሕይወትን ፡ ይውሰዱ
ስምህ ፡ ይቀደስ ፣ ሃሌሉያ!