ኃጢአትህ ፡ ቢቀላብህ (Hatiateh Biqelabeh)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ኃጢአትህ ፡ ቢቀላብህ ፡ እንደ ፡ በረዶ ፡ ይነፃል (፪x)
ግን ፡ ቢቀላ ፡ (ግን ፡ ቢቀላ ፡ እንደ ፡ ደም)
እንደ ፡ ደም ፡ እንደ ፡ ጥጥ ፡ ነጻ
ኃጢአትህ ፡ ቢቀላብህ (፪x)
እንደ ፡ በረዶ ፡ ይነጻል (፪x)

አሁንም ፡ ቃሉን ፡ ሥሙ ፡ ወደ ፡ አምላክ ፡ ተመለሱ (፪x)
ግሩም ፡ ፈቃር ፡ ነው ፡ (ግን ፡ እንደ ፡ ደም ፡ ቢቀላ)
ጌታችንን ፡ አድምጹ ፡ ቃሉን
አሁንም ፡ ቃሉን ፡ ሥሙ (፪x)
ወደ ፡ አምላክ ፡ ተመለሱ (፪x)

ይምራል ፡ ኃጢአታችንን ፡ ሁለተኛ ፡ አያስብም (፪x)
ሕዝቤ ፡ ሆይ ፡ ኑ ፡ (ግን ፡ እንደ ፡ ደም ፡ ቢቀላ)
ወደ ፡ እኔ ፡ ይጠራል ፡ አምላክ
ይምራል ፡ ኃጢአታችን (፪x)
ሁለተኛ ፡ አያስብም (፪x)