ጉልበት ፡ ለሞላው ፡ ስምህ (Gulbet Lemolaw Semeh)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

1. የዘለዓለም ፡ ንጉሥ ፡ የሕይወት ፡ እንባ
በጠላት ፡ ፊት ፡ ለፊት ፡ ዘይት ፡ የምትቀባ
በምድር ፡ በዳ ፡ ዘይት ፡ አዘጋጅተህ
በተራሮች ፡ ላይ ፡ ታስኬደናለህ

አዝ፦ ጉልበት ፡ ለሞላው ፡ ስምህ
ድንቅም ፡ ለሆነው ፡ ስምህ
መካር ፡ ለሆነው ፡ ስምህ ፡ ክብር ፡ ይሁን
ፍቅር ፡ ለሞላው ፡ ስምህ

2. የዘወትር ፡ ጥላ ፡ ኃያል ፡ እግዚአብሔር
በአንተ ፡ ተማምኖ ፡ ጸንቶ ፡ ለሚኖር
ከሰላምህ ፡ ምንጭ ፡ ታጠጣዋለህ
በክንፍህ ፡ ጥላ ፡ ታስረዳዋለህ

አዝ፦ ጉልበት ፡ ለሞላው ፡ ስምህ
ድንቅም ፡ ለሆነው ፡ ስምህ
መካር ፡ ለሆነው ፡ ስምህ ፡ ክብር ፡ ይሁን
ፍቅር ፡ ለሞላው ፡ ስምህ

3. ለሚታመኑህ ፡ አውቀው ፡ ስምህን
አትጥልምና ፡ አንተን ፡ ሚሹህን
ጌታ ፡ በህዝብህ ፡ ላይ ፡ ዐይኖችህ ፡ ናቸው
ከአንተ ፡ ሊኖሩ ፡ ልትጠብቃቸው

አዝ፦ ወገን ፡ ለሆነው ፡ ስምህ
ሰብሳቢ ፡ ለሆነው ፡ ስምህ
ምገስ ፡ ለሞላው ፡ ስምህ ፡ ክብር ፡ ይሁን
ውበት ፡ ለሞላው ፡ ስምህ
ቅባት ፡ ለሆነው ፡ ስምህ
ምርኩዝ ፡ ለሆነው ፡ ስምህ ፡ ክብር ፡ ይሁን

4. ከሁሉም ፡ ይልቅ ፡ የፍቅር ፡ ነገር
አይሎ ፡ ረዳን ፡ ልንሆን ፡ ከአንተ ፡ ጋር
ከውሽንፍርና ፡ ከአውሎ ፡ ንፋስ
ልንተርፍ ፡ አበቃን ፡ እዚህ ፡ እንድንደርስ

አዝ፦ ወገን ፡ ለሆነው ፡ ስምህ
ሰብሳቢ ፡ ለሆነው ፡ ስምህ
ምገስ ፡ ለሞላው ፡ ስምህ ፡ ክብር ፡ ይሁን
ውበት ፡ ለሞላው ፡ ስምህ
ቅባት ፡ ለሆነው ፡ ስምህ
ምርኩዝ ፡ ለሆነው ፡ ስምህ ፡ ክብር ፡ ይሁን