ጊዜ ፡ ይመሻል (Gizie Yimeshal)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ጊዜ ፡ ይመሻል ፡ ጌታ ፡ ሆይ!
አትሂድብን ፡ በዚህ ፡ ቆይ
የቅዱስ ፡ ዕውነትህ ፡ ብርሃን
ይገለጥ ፡ ለምዕመናን

የሚያሳዝን ፡ ዘመን ፡ ነው
ተማሮችህን ፡ አትተው
እስክንሞት ፡ ትምህርትህን
አቤቱ ፡ አትከልክለን

ክፋቱ ፡ በዛ ፡ አምላክ ፡ ሆይ!
የቤትህን ፡ መጨነቅ ፡ እይ
የቃልህ ፡ ጣዕም ፡ ሊታወቀን
የመንፈስህን ፡ ኃይል ፡ ስጠን

ነፍሣችንን ፡ ሊገድላት
ይጥራል ፡ ሰይጣን ፡ በትጋት
አገልጋዮቹም ፡ ቃልህን
ይቃወማሉ ፡ ሌት ፡ ተቀን

በዚህም ፡ ከኛ ፡ አትለይ
ትረዳን ፡ ዘንድ ፡ አትዘግይ
ረድዔትህም ፡ እንዳለነ
በድንቅ ፡ ሥራህ ፡ አሳየነ

ይህ ፡ ነው ፡ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ጉዳይህ
ክብርንም ፡ ሁሉ ፡ እንስጥህ
ና ፡ ተንከባከበብ ፡ መንጋህን
ከቅዱስ ፡ ቃልህ ፡ መግበን

በጻሩና ፡ በመከራው
መድኃኒት ፡ ቃልህ ፡ ብቻ ፡ ነው
በብርቱ ፡ ችግራችንም
አምባችን ፡ ነው ፡ ዕርዳችንም

ከዓለም ፡ ጨለማ ፡ ምራን
ወደ ፡ ቤታችንም ፡ አግባን
ከእንባ ፡ ዱኃ ፡ አሻግረን
በዕቅፍህም ፡ አሳርፈን