ጊዜ ፡ የማይለውጥህ ፡ የእኔ ፡ ጌታ (Gizie Yemayleweteh Yenie Gieta)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

1. ያ ፡ የለቅሶ ፡ ጊዜ ፡ የዋይታ
በአንተ ፡ የተለወጠው ፡ በደስታ
የሃዘኑን ፡ ጊዜ ፡ አስረሳኝ
የጌታዬ ፡ ፍቅሩ ፡ ሲነካኝ (፫x)

አዝ፦ ጊዜ ፡ የማይለውጥህ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ለማንም ፡ ለምንም ፡ የማትረታ
ከልቤ ፡ እወድሃለሁ ፡ ኢየሱስ
አንተ ፡ ነህ ፡ የሕይወቴ ፡ ንጉሥ

2. ሕይወቴ ፡ ተሞልቶ ፡ በክፋት
ተለውሼ ፡ ሳለሁ ፡ ባኀጢአት
ዐይንም ፡ እንኳን ፡ አይቶ ፡ አልራራልኝ
ጌታዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ሲያገኘኝ (፫x)

አዝ፦ ጌታ ፡ ለኛ ፡ ያደረገው ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው
አቤት ፡ ስንቱን ፡ አልፈን ፡ በእርሱ ፡ ችለነው
ብርታት ፡ ጉልበት ፡ ሆነልን
ስሙ ፡ ከፍ ፡ ይበልልን

3. መኖር ፡ አቁሜያለሁ ፡ በመላ
ማንም ፡ አይገዛኝም ፡ ከአንተ ፡ ሌላ
ተረትቻለሁኝ ፡ በፍቅርህ
አባቴ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ እኔም ፡ ልጅህ (፫x)