From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
አዝ ፣
ጊዜ ፡ አይሽረውም ፡ የማመልከው
ሙት ፡ አምላክ ፡ አይደለም ፡ የማምነው
አልፋ ፡ ዖሜጋ ፡ የሆነው
በከበረው ፡ ሥፍራ ፡ የሚኖረው
ሕያው ፡ ጌታ ፡ በላይ ፡ ያለው ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው
እመካበታለሁ ፡ ይህን ፡ ሕያው ፡ ጌታ
ብርቱ ፡ ክንድ ፡ ስላለው ፡ ጠላትን ፡ ሊረታ
በእርሱ ፡ የታመነ ፡ ማንም ፡ አላፈረም
መጽናናት ፡ በረከት ፡ ከቤቱ ፡ አልጠፋም
አዝ ፣
ጊዜ ፡ አይሽረውም ፡ የማመልከው
ሙት ፡ አምላክ ፡ አይደለም ፡ የማምነው
አልፋ ፡ ዖሜጋ ፡ የሆነው
በከበረው ፡ ሥፍራ ፡ የሚኖረው
ሕያው ፡ ጌታ ፡ በላይ ፡ ያለው ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው
ኧረ ፡ ማን ፡ አፈረ ፡ የጌታን ፡ ሥም ፡ ጠርቶ?
ከቶ ፡ ማን ፡ ወደቀ ፡ በጠላት ፡ ተረትቶ?
ድል ፡ አድራጊው ፡ አምላክ ፡ ሁሌ ፡ እያሸነፈ
ሕዝቡን ፡ ያሻግራል ፡ በድል ፡ እያለፈ
አዝ ፣
ጊዜ ፡ አይሽረውም ፡ የማመልከው
ሙት ፡ አምላክ ፡ አይደለም ፡ የማምነው
አልፋ ፡ ዖሜጋ ፡ የሆነው
በከበረው ፡ ሥፍራ ፡ የሚኖረው
ሕያው ፡ ጌታ ፡ በላይ ፡ ያለው ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው
የዘላለም ፡ አምላክ ፡ ሕያው ፡ ሆኖ ፡ ያለው
ሁሉን ፡ እንደ ፡ ሃሣቡ ፡ አድርጐ ፡ የፈጠረው
በከበረው ፡ ሥፍራ ፡ በላይ ፡ የሚኖረው
ዛሬም ፡ ሆነ ፡ ነገ ፡ ትምክህቴ ፡ እርሱ ፡ ነው
አዝ ፣
ጊዜ ፡ አይሽረውም ፡ የማመልከው
ሙት ፡ አምላክ ፡ አይደለም ፡ የማምነው
አልፋ ፡ ዖሜጋ ፡ የሆነው
በከበረው ፡ ሥፍራ ፡ የሚኖረው
ሕያው ፡ ጌታ ፡ በላይ ፡ ያለው ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው
|