ጌታዬ ፡ መታመኛዬ (Gietayie Metamegnayie)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ጌታዬ ፡ መታመኛዬ ፡ ጌታዬ (፮x)

ያስጨናቂዎቼን ፡ አይቶ ፡ ፉከራ (፪x)
በሞት ፡ እንዳልተኛ ፡ ዓይኖቼን ፡ አበራ

ኧረ ፡ እሱስ ፡ መድኃኒቴ ፡ ነው ፡ ኧረ ፡ እሱስ (፪x)
ኢየሱስ ፡ መድኃኒቴ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ (፪x)

ምን ፡ ልክፈለው ፡ ምንን ፡ ልስጠው ፡ ውለታው ፡ ከአዕምሮ ፡ በላይ ፡ ነው (፪x)

ኧረ ፡ እሱስ ፡ መድኃኒቴ ፡ ነው ፡ ኧረ ፡ እሱስ (፪x)
ኢየሱስ ፡ መድኃኒቴ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ (፪x)

ከኃያላን ፡ መሃል ፡ ኃያል ፡ አደረገኝ
ከብርቱዎች ፡ መሃል ፡ ብርታት ፡ አስታጠቀኝ
ከአሸናፊዎች ፡ ሁሉ ፡ በላይ ፡ አደረገኝ
የጠላቴን ፡ አንገት ፡ ጌታ ፡ አስረገጠኝ

ኧረ ፡ እሱስ ፡ መድኃኒቴ ፡ ነው ፡ ኧረ ፡ እሱስ (፪x)
ኢየሱስ ፡ መድኃኒቴ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ (፪x)

በሞት ፡ ጥላ ፡ ብሄድ ፡ ክፉን ፡ አልፈራም (፪x)
ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ያለው ፡ ለጠላቴ ፡ አይራራም

ስጠራው ፡ ፈጥኖ ፡ እየመጣ
ከፊቴ ፡ ቀድሞ ፡ እየወጣ
እርሱ ፡ በእኔ ፡ በእርሱ ፡ አይረታም
ጠላቶቼን ፡ ሁሉ ፡ አሳፍሯል (፪x)

ጌታዬ ፡ መታመኛዬ ፡ ጌታዬ (፮x)