ጌታዬ ፡ በአንተ ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁና (Gietayie Beante Sew Hognalehuna)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ጌታዬ ፡ በአንተ ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁና
እስኪ ፡ ልሰዋልህ ፡ ክብር ፡ ምሥጋና
እንባዬን ፡ ጠርገህ ፡ ማቄን ፡ ቀደሃል
ሃዘን ፡ ምሬቴን ፡ ከእኔ ፡ ወስደሃል

1. ከታላላቆች ፡ ካለቆች ፡ ጋራ
ፊት ፡ ለፊት ፡ ቆሜ ፡ እኩል ፡ ሳወራ
ስለሆንክልኝ ፡ ግርማ ፡ ሞገሴ
ከፍ ፡ በልልኝ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱሴ

አዝ፦ ጌታዬ ፡ በአንተ ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁና
እስኪ ፡ ልሰዋልህ ፡ ክብር ፡ ምሥጋና
እንባዬን ፡ ጠርገህ ፡ ማቄን ፡ ቀደሃል
ሃዘን ፡ ምሬቴን ፡ ከእኔ ፡ ወስደሃል

2. መልስ ፡ ሆነኅኛል ፡ ከሰቆቃዬ
በአንተ ፡ መጽናናት ፡ ደርቋል ፡ እንባዬ
አቁመኸኛል ፡ በተራራ ፡ ላይ
አብቅተኸኛል ፡ ክብርህን ፡ እንዳይ

አዝ፦ ጌታዬ ፡ በአንተ ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁና
እስኪ ፡ ልሰዋልህ ፡ ክብር ፡ ምሥጋና
እንባዬን ፡ ጠርገህ ፡ ማቄን ፡ ቀደሃል
ሃዘን ፡ ምሬቴን ፡ ከእኔ ፡ ወስደሃል

3. በአንተ ፡ ለምልሟል ፡ ምድረ ፡ በዳዬ
በረከት ፡ ሞልቷል ፡ የሕይወት ፡ ጓዳዬ
ላይ ፡ ታች ፡ ከማለት ፡ ከሩጫ ፡ አርፌ
መብላት ፡ ጀመርኩኝ ፡ እሸት ፡ ቀጥፌ

አዝ፦ ጌታዬ ፡ በአንተ ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁና
እስኪ ፡ ልሰዋልህ ፡ ክብር ፡ ምሥጋና
እንባዬን ፡ ጠርገህ ፡ ማቄን ፡ ቀደሃል
ሃዘን ፡ ምሬቴን ፡ ከእኔ ፡ ወስደሃል

4. ዛሬ ፡ ጠላቴ ፡ ስፍራውን ፡ ለቋል
ከላይ ፡ የነበር ፡ ከእግሬ ፡ ስር ፡ ወድቋል
በአንተ ፡ ጀግንነት ፡ ነጻ ፡ ወጣሁኝ
አንተም ፡ ስትከብር ፡ እኔም ፡ ከበርኩኝ

አዝ፦ ጌታዬ ፡ በአንተ ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁና
እስኪ ፡ ልሰዋልህ ፡ ክብር ፡ ምሥጋና
እንባዬን ፡ ጠርገህ ፡ ማቄን ፡ ቀደሃል
ሃዘን ፡ ምሬቴን ፡ ከእኔ ፡ ወስደሃል