ጌታን ፡ ባርኪው ፡ ነፍሴ (Gietan Barkiw Nefsie)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አዝጌታን ፡ ባርኪው ፡ ነፍሴ (፪x)
ኀጢአትሽን ፡ ይቅር ፡ ይላል
ደዌሽንም ፡ ሁሉ ፡ ይፈውሳል
ነፍሴ ፡ ጌታን ፡ ዘወትር ፡ ባርኪው

1. ሕይወትሽን ፡ ከክፉ ፡ የሚያድናት
ምኞትሽን ፡ የሚያጠግባት
ባርኮቱንም ፡ የሚያፈስልሽን
ነፍሴ ፡ ጌታን ፡ ዘወትር ፡ ባርኪው

አዝጌታን ፡ ባርኪው ፡ ነፍሴ (፪x)
ኀጢአትሽን ፡ ይቅር ፡ ይላል
ደዌሽንም ፡ ሁሉ ፡ ይፈውሳል
ነፍሴ ፡ ጌታን ፡ ዘወትር ፡ ባርኪው

2. በምህረቱና ፡ በቸርነቱ
ከጥልቅ ፡ ረግረግ ፡ ያወጣሽን
በሕያዋን ፡ መዝገብ ፡ ያጻፈሽን
ነፍሴ ፡ ጌታን ፡ ዘወትር ፡ ባርኪው

አዝጌታን ፡ ባርኪው ፡ ነፍሴ (፪x)
ኀጢአትሽን ፡ ይቅር ፡ ይላል
ደዌሽንም ፡ ሁሉ ፡ ይፈውሳል
ነፍሴ ፡ ጌታን ፡ ዘወትር ፡ ባርኪው

3. ስብራትህን ፡ የሚጠግነው
ጭንቀትሽን ፡ የሚያጠፋው
በመከራው ፡ ፈጥኖ ፡ የሚረዳሽ
ነፍሴ ፡ ጌታን ፡ ዘወትር ፡ ባርኪው

አዝጌታን ፡ ባርኪው ፡ ነፍሴ (፪x)
ኀጢአትሽን ፡ ይቅር ፡ ይላል
ደዌሽንም ፡ ሁሉ ፡ ይፈውሳል
ነፍሴ ፡ ጌታን ፡ ዘወትር ፡ ባርኪው