ጌታችን ፡ ና ፡ ና (Gietachen Na Na)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ና ፡ ና ፡ ጌታችን ፡ ና ፡ ና
ዳመናትን ፡ ሰንጥቀህ ፡ ውረድ
ለእኛ ፡ ተዋጋ
የዲያብሎስን ፡ ሥራ ፡ አፈራርስ

ቀስትህን ፡ ወርውር ፡ ጠላትህን ፡ ውጋ
የዲያብሎስን ፡ ሥራ ፡ ሃሣቡን ፡ አናጋ
ኃይላችን ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ጉልበታችን
ቅደምልን ፡ ጌታ ፡ ከፊት ፡ ፊታችን

አዝ፦ ና ፡ ና ፡ ጌታችን ፡ ና ፡ ና
ዳመናትን ፡ ሰንጥቀህ ፡ ውረድ
ለእኛ ፡ ተዋጋ
የዲያብሎስን ፡ ሥራ ፡ አፈራርስ

ሰይፍህን ፡ ምዘዝ ፡ ኃይልህ ፡ ይገለጥ
እሣትህን ፡ አውርድ ፡ ጠላታችን ፡ ይቅለጥ
በስምህ ፡ ወጥተናል ፡ ወደ ፡ ጽዮን
በደምህ ፡ ቅጠረን ፡ አንተ ፡ ምራን

አዝ፦ ና ፡ ና ፡ ጌታችን ፡ ና ፡ ና
ዳመናትን ፡ ሰንጥቀህ ፡ ውረድ
ለእኛ ፡ ተዋጋ
የዲያብሎስን ፡ ሥራ ፡ አፈራርስ

ከአንተ ፡ እንጠብቃለን ፡ ከታላቁ ፡ ክንድህ
የአጋንንትም ፡ ጭፍሮች ፡ ይውደቁ ፡ በእጅህ
መሠረታችን ፡ ሁን ፡ ምሰሶያችን
እስክንገባ ፡ ጽዮን ፡ አገራችን

አዝ፦ ና ፡ ና ፡ ጌታችን ፡ ና ፡ ና
ዳመናትን ፡ ሰንጥቀህ ፡ ውረድ
ለእኛ ፡ ተዋጋ
የዲያብሎስን ፡ ሥራ ፡ አፈራርስ