ጌታችንን ፡ አመስግኑት (Gietachenen Amesgenut)
From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
ጌታችን ፡ አመስግኑት ፡ በደስታ ፡ ዝማሬ
ሕጻናት ፡ ያመስግኑት ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታችንን
ታናሾችን ፡ ወደደ ፡ ወደርሱም ፡ ጠራቸው
በክንዱም ፡ አቀፋቸው ፡ ነፍሱንም ፡ ሰጣቸው
ጐልማሶች ፡ ያመስግኑህ ፡ ቅኔም ፡ ይቀኙልህ
ንጹህ ፡ ያለ ፡ ኃጢአት ፡ በምድር ፡ የነበርህ
መታዘዝ ፡ አስተምረን ፡ ክፉን ፡ እንድንሸሽ
በሰማያዊ ፡ መቅደስ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ እንድንሆን
ሴቶችም ፡ ያመስግኑህ ፡ አንተ ፡ የድንግል ፡ ልጅ
ፀጋና ፡ ትህትና ፡ ሕይወትን ፡ የተሞላህ
ፀጋህን ፡ አልብሳቸው ፡ ሰላምህን ፡ ስጣቸው
በፊትህ ፡ የሚያበራ ፡ እምነት ፡ ላክላቸው
በአንድነት ፡ ተባብረን ፡ ለአንተ ፡ እንቀኝልህ
ብርሃን ፡ መሪ ፡ ሁንልን ፡ በልጅነታችን
ወደ ፡ ላይም ፡ ምራነ ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ ሳለን
እንዳንተ ፡ እንድንሆን ፡ በጥበብህ ፡ አድገን
|