ጌታ ፡ የእኛ ፡ እድል ፡ ፈንታ ፡ ነው (Gieta Yegna Edel Fenta New)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

1. ሕይወት ፡ ተገላቢጦሽ ፡ ሲሆን ፡ ተመስገን
ደስታ ፡ ለሓሰተኞች ፡ ስትሆን ፡ ተመስገን
ሃዘን ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ሲበረታ ፡ ተመስገን
ጉልበት ፡ በዝለትም ፡ ሲረታ ፡ ተመስገን
በዚህ ፡ ሁሉ ፡ ግን ፡ አለህ ፡ አብረኸን
ስንደካክም ፡ ብርታት ፡ ሆነኸን
ከኃይል ፡ ወደኃይል ፡ አሸጋገርኸን
እዚህ ፡ ደርሰናል ፡ ተሸክመኸን (፪x)

አዝ፦ ጌታ ፡ የእኛ ፡ ዕድል ፡ ፈንታ
ፍጽም ፡ የማትረታ
ስንደክም ፡ ስንበረታ
በዚህ ፡ ሁሉ ፡ ግን ፡ አለህ ፡ አብረኸን
እናመሰግንሃለን

2. መከራ ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ሲደርስብን ፡ ተመስገን
ጠላትም ፡ ሲያጠፋን ፡ ሲዝትብን ፡ ተመስገን
በአውሎ ፡ ንፋስ ፡ ስትናወጥ ፡ ታንኳችን ፡ ተመስገን
መልስህ ፡ ስታጽናናን ፡ ጌታችን ፡ ተመስገን
በዚህ ፡ ሁሉ ፡ ግን ፡ አለህ ፡ አብረኸን
ስንደካክም ፡ ብርታት ፡ ሆነኸን
ከኃይል ፡ ወደኃይል ፡ አሸጋገርኸን
እዚህ ፡ ደርሰናል ፡ ተሸክመኸን (፪x)

አዝ፦ ጌታ ፡ የእኛ ፡ ዕድል ፡ ፈንታ
ፍጽም ፡ የማትረታ
ስንደክም ፡ ስንበረታ
በዚህ ፡ ሁሉ ፡ ግን ፡ አለህ ፡ አብረኸን
እናመሰግንሃለን

3. ዘይትህ ፡ በእጅጉ ፡ ሞልቶ ፡ ሲፈስ ፡ ተመስገን
ከእኛ ፡ አልፎ ፡ ሌሎችንም ፡ ሲፈውስ ፡ ተመስገን
ዲያቢሎስ ፡ ስንፈቱንም ፡ ሲጐነኝ ፡ ተመስገን
በዚህ ፡ ሁሉ ፡ ግን ፡ አለህ ፡ አብረኸን
ስንደካክም ፡ ብርታት ፡ ሆነኸን
ከኃይል ፡ ወደኃይል ፡ አሸጋገርኸን
እዚህ ፡ ደርሰናል ፡ ተሸክመኸን (፪x)

አዝ፦ ጌታ ፡ የእኛ ፡ ዕድል ፡ ፈንታ
ፍጽም ፡ የማትረታ
ስንደክም ፡ ስንበረታ
በዚህ ፡ ሁሉ ፡ ግን ፡ አለህ ፡ አብረኸን
እናመሰግንሃለን

4. ወዳች ፡ ነው ፡ ያሉት ፡ ሁሉ ፡ ሲርቅ ፡ ተመስገን
ከጠላት ፡ አብሮ ፡ እኛን ፡ ሲንቅ ፡ ተመስገን
ሁሉ ፡ በጊዜው ፡ ሲፈራረቅ ፡ ተመስገን
አንተ ፡ አለኸን ፡ በጭራሽ ፡ የማትርቅ ፡ ተመስገን
በዚህ ፡ ሁሉ ፡ ግን ፡ አለህ ፡ አብረኸን
በድካማችን ፡ ብርታት ፡ ሆነኸን

አዝ፦ ጌታ ፡ የእኛ ፡ ዕድል ፡ ፈንታ
ፍጽም ፡ የማትረታ
ስንደክም ፡ ስንበረታ
በዚህ ፡ ሁሉ ፡ ግን ፡ አለህ ፡ አብረኸን
እናመሰግንሃለን