ጌታ ፡ ቅደምልኝ (Gieta Qedemelegn)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

1. ጌታን ፡ የሚያስቀድም ፡ በኑሮ ፡ በቤቱ
አቅፎ ፡ እንዲደግፈው ፡ እንደናት ፡ አባቱ
ያ ፡ ነው ፡ ያምላክ ፡ ወዳጅ ፡ ክብሩን ፡ የማይፈልግ
በክፉ ፡ በደጉ ፡ ከቶ ፡ የማይበረግግ

አዝ፦ ጌታ ፡ ቅደምልኝ ፡ በኑሮዬ ፡ ሁሉ
ያንተ ፡ ስለሆነ ፡ በመከራ ፡ ድሉ

2. በትዕግሥት ፡ ጠብቆ ፡ አምላክ ፡ ይቅደም ፡ የሚል
እራሱን ፡ በውርደት ፡ ከመስቀሉ ፡ የሚጥል
ያ ፡ ነው ፡ ያምላክ ፡ ወዳጅ ፡ ምኞቱን ፡ ያሟላ
ለያዘው ፡ ቁም ፡ ነገር ፡ ከቶ ፡ የማይላላ

አዝ፦ ጌታ ፡ ቅደምልኝ ፡ በኑሮዬ ፡ ሁሉ
ያንተ ፡ ስለሆነ ፡ በመከራ ፡ ድሉ

3. ጌታ ፡ እንዲቀድምለት ፡ በኑሮ ፡ መከራ
በእንባ ፡ እየታጀበ ፡ በመዝሙር ፡ ሲጣራ
ያ ፡ ነው ፡ ያምላክ ፡ ወዳጅ ፡ ክብሩን ፡ የሰቀለ
የአጋንንት ፡ ሥልጣን ፡ በእንባው ፡ ያቃለለ

አዝ፦ ጌታ ፡ ቅደምልኝ ፡ በኑሮዬ ፡ ሁሉ
ያንተ ፡ ስለሆነ ፡ በመከራ ፡ ድሉ