ጌታ ፡ ለኛ ፡ ያደረገው (Gieta Legna Yaderegew)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

1. የማይቻለው ፡ በእርሱ ፡ ተችሎ
ሲዝት ፡ ሲፎክር ፡ ስንቱ ፡ ተጥሎ
በሚያበረታው ፡ ጌታ ፡ በርትተን
እዚህ ፡ ደርሰናል ፡ ሁሉንም ፡ አልፈን

አዝ፦ ጌታ ፡ ለኛ ፡ ያደረገው ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው
አቤት ፡ ስንቱን ፡ አልፈን ፡ በእርሱ ፡ ችለነው
ብርታት ፡ ጉልበት ፡ ሆነልን
ስሙ ፡ ከፍ ፡ ይበልልን

2. ባሕር ፡ ሞገዱን ፡ በስልጣን ፡ አዝዞ
በፍቅር ፡ እጁ ፡ እጃችንን ፡ ይዞ
ከዘመን ፡ ዘመን ፡ አሸጋግሮናል
ክብር ፡ ለስሙ ፡ ይሁን ፡ ብለናል

አዝ፦ ጌታ ፡ ለኛ ፡ ያደረገው ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው
አቤት ፡ ስንቱን ፡ አልፈን ፡ በእርሱ ፡ ችለነው
ብርታት ፡ ጉልበት ፡ ሆነልን
ስሙ ፡ ከፍ ፡ ይበልልን

3. ብችኞች ፡ መስለን ፡ ረዳት ፡ የሌለን
ስንቱ ፡ ሲቃጣ ፡ ይዞ ፡ ሊያስርቀን
የነአብርሃም ፡ የይስሓቅ ፡ አምላክ
በድል ፡ መርቶናል ፡ ስሙ ፡ ይባረክ

አዝ፦ ጌታ ፡ ለኛ ፡ ያደረገው ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው
አቤት ፡ ስንቱን ፡ አልፈን ፡ በእርሱ ፡ ችለነው
ብርታት ፡ ጉልበት ፡ ሆነልን
ስሙ ፡ ከፍ ፡ ይበልልን

4. ስንቱ ፡ ታለፈ ፡ ተረግጦ ፡ በእግር
ላይንሰራራ ፡ ዳግመኛ ፡ ላይኖር
የአንበሳውን ፡ መንጋጋ ፡ ዘግቶ
አቆመን ፡ ጌታ ፡ ፀጋውን ፡ ሞልቶ

አዝ፦ ጌታ ፡ ለኛ ፡ ያደረገው ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው
አቤት ፡ ስንቱን ፡ አልፈን ፡ በእርሱ ፡ ችለነው
ብርታት ፡ ጉልበት ፡ ሆነልን
ስሙ ፡ ከፍ ፡ ይበልልን