From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
ጌታ ፡ ከሞት ፡ ተነሥቷል
መቃብር ፡ አሁን ፡ በራ
የሞትን ፡ ኃይል ፡ አሸንፏል
ሕይወትንም ፡ አሰፋ
ከመቃብር ፡ ይወጣል
በወንጌሉ ፡ ተጽፏል
ትንሣዔ ፡ ነኝ ፡ ሕይወትም
ሃሌ ፡ ሉያ !
ወደ ፡ ሕይወት ፡ አካሄዴን
በእርሱ ፡ ተስፋ ፡ ላቀና
ልነሣ ፡ ነኝ ፡ በፍርድ ፡ ቀን
ልኖር ፡ ለርሱ ፡ ምሥጋና
በማይጠፋብኝ ፡ ሕይወት
ከንቱነት ፡ የማይነካበት
በኃጢአት ፡ የማይረክስ
ሃሌ ፡ ሉያ !
ሞት ፡ ሆይ! የታለ ፡ የአንተ ፡ እሾህ?
ማሸነፍህ ፡ የታለ?
ኢየሱስ ፡ ፍፁም ፡ ካሸነፈህ
የሚጐዳኝ ፡ ማን ፡ አለ?
ለዘለዓለም ፡ የእርሱ ፡ ነኝ
ይላል ፡ እኔ ፡ ወዳለሁኝ
እናንትም ፡ ልትሆኑ
ሃሌ ፡ ሉያ !
|