ጌታ ፡ ፍቅርህን ፡ የሚነግረኝ (Gieta FeqrehenYeminegregn)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ጌታ ፡ ፍቅርህን ፡ የሚነግረኝ
ድምጽህን ፡ እሰማለሁ
የአንተ ፡ ገንዘብ ፡ ነኝ
አንተም ፡ ጠብቀኝ
ፀጋህን ፡ እመኛለሁ
ወደ ፡ አንተ ፡ ኢየሱስ ፡ አቅርበኝ
ሳበኝ ፡ ወደ ፡ መስቀልህ
በተወጋውም ፡ ጐድንህ
ወትሮ ፡ ሠውረኝ
ሳበኝ ፡ ወደ ፡ መስቀልህ

ላገልግልህ ፣ አምላክ ፡ ቀድሰኝ
ባምላካዊ ፡ ኃይልም ፡ ና
ታላቅ ፡ ፍቅርህም ፡ ፀጋህን ፡ ይስጠኝ
ከአንተ ፡ ዘንድ ፡ ወትሮ ፡ ልጽና
ወደ ፡ አንተ ፡ ኢየሱስ ፡ አቅርበኝ
ሳበኝ ፡ ወደ ፡ መስቀልህ
በተወጋውም ፡ ጐድንህ
ወትሮ ፡ ሠውረኝ
ሳበኝ ፡ ወደ ፡ መስቀልህ

ኦ ፡ መድኃኒቴ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ስገኝ
በእግርህ ፡ ተንበርክኬ
ፊትህንም ፡ ሳይ ፡ እኔ ፡ ብጹዕ ፡ ነኝ
ከአንተ ፡ ዘንድ ፡ ኦ ፡ አምላኬ
ወደ ፡ አንተ ፡ ኢየሱስ ፡ አቅርበኝ
ሳበኝ ፡ ወደ ፡ መስቀልህ
በተወጋውም ፡ ጐድንህ
ወትሮ ፡ ሠውረኝ
ሳበኝ ፡ ወደ ፡ መስቀልህ

ግን ፡ የሞትን ፡ ባሕር ፡ ተሻግሬ
ፍቅርህ ፡ ለእኔ ፡ ግልጥ ፡ ሲሆን
አዲስ ፡ መዝሙሩን ፡ ለአንተ ፡ ዘምሬ
የሚሆነኝ ፡ ምን ፡ ይሆን?
ወደ ፡ አንተ ፡ ኢየሱስ ፡ አቅርበኝ
ሳበኝ ፡ ወደ ፡ መስቀልህ
በተወጋውም ፡ ጐድንህ
ወትሮ ፡ ሠውረኝ
ሳበኝ ፡ ወደ ፡ መስቀልህ