From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
አዝ፦ ጌታ ፡ ኢየሱሴ ፡ የናዝሬቱ ፡ መልካም
ልቤ ፡ ወደደህ ፡ አፈቀረህ ፡ በጣም
ከእጆችህ ፡ መዳፍ ፡ ምን ፡ ጊዜም ፡ አልወጣም
1. ነበልባል ፡ ዐይኖችህ ፡ ምንጊዜም ፡ ስራቸው
እኔን ፡ መንከባከብ ፡ እኔን ፡ መጠበቅ ፡ ነው
ጠላቴም ፡ አየና ፡ እንዳለኝ ፡ ረጂ
ሊያጠፋኝ ፡ አልቻለም ፡ በምኞት ፡ ቀረ ፡ እንጂ
አዝ፦ ጌታ ፡ ኢየሱሴ ፡ የናዝሬቱ ፡ መልካም
ልቤ ፡ ወደደህ ፡ አፈቀረህ ፡ በጣም
ከእጆችህ ፡ መዳፍ ፡ ምን ፡ ጊዜም ፡ አልወጣም
2. የእጆችህ ፡ መዳፍ ፡ አጥብቀው ፡ ይዘውኛል
ለጠላት ፡ መንጋጋ ፡ መቼ ፡ ይሰጡኛል
ይህን ፡ ሳይ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ዛሬ፡ ከበፊቱ
ሬት ፡ የሆነብኝ ፡ ከአንተ ፡ መለየቱ
አዝ፦ ጌታ ፡ ኢየሱሴ ፡ የናዝሬቱ ፡ መልካም
ልቤ ፡ ወደደህ ፡ አፈቀረህ ፡ በጣም
ከእጆችህ ፡ መዳፍ ፡ ምን ፡ ጊዜም ፡ አልወጣም
3. በዓለም ፡ ፈተና ፡ ወይም ፡ በሥጋዬ
በጥፋት ፡ ውስጥ ፡ ሆኜ ፡ አልታዘዝ ፡ ብዬ
ጥፋተኛነቴን ፡ ባውቀው ፡ ባላውቀውም
ጉስቁል ፡ ብዬ ፡ ስታይ ፡ አልፈኸኝ ፡ አታውቅም
አዝ፦ ጌታ ፡ ኢየሱሴ ፡ የናዝሬቱ ፡ መልካም
ልቤ ፡ ወደደህ ፡ አፈቀረህ ፡ በጣም
ከእጆችህ ፡ መዳፍ ፡ ምን ፡ ጊዜም ፡ አልወጣም
4. ላንተው ፡ ባለኝ ፡ ፍቅር ፡ ሳደንቅ ፡ ጓጉቼ
እይልኝ ፡ ስጨነቅ ፡ ቃላቶቼን ፡ አጥቼ
ቃላቶች ፡ ቢያጥሩኝም ፡ ብቻ ፡ ተመስገን ፡ ነው
ኢየሱስን ፡ የሰጠኝ ፡ እግዚአብሔር ፡ ፍቅር ፡ ነው
አዝ፦ ጌታ ፡ ኢየሱሴ ፡ የናዝሬቱ ፡ መልካም
ልቤ ፡ ወደደህ ፡ አፈቀረህ ፡ በጣም
ከእጆችህ ፡ መዳፍ ፡ ምን ፡ ጊዜም ፡ አልወጣም
|