ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ እጄን ፡ ያዘኝ (Gieta Eyesus Hoy Ejien Yazegne)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

1. የማደርገው ፡ ሲገባኝ ፡ ግራ
ኑሮ ፡ ሲሆንብኝ ፡ መራራ
የምትጣፍጥ ፡ ጨው ፡ ቅመሜ
ፍቀህ ፡ አትቁም ፡ ከአጠገቤ
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ እጄን ፡ ያዘኝ

አዝ፦ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ እጄን ፡ ያዘኝ
የማልረባ ፡ ነኝ ፡ ኃይል ፡ የሌለኝ
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ እጄን ፡ ያዘኝ
የማልረባ ፡ ደካማ ፡ ነኝ

2. እኔ ፡ የያዝኩ ፡ እንደሁ ፡ እጅህን
መቀጠል ፡ ሲያቅተኝ ፡ እርምጃዬን
ድንገት ፡ እለቅሃለሁ ፡ ደካማ ፡ ነኝ
አንተ ፡ አትደክምም ፡ እጄን ፡ ያዘኝ
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ እጄን ፡ ያዘኝ

አዝ፦ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ እጄን ፡ ያዘኝ
የማልረባ ፡ ነኝ ፡ ኃይል ፡ የሌለኝ
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ እጄን ፡ ያዘኝ
የማልረባ ፡ ደካማ ፡ ነኝ

3. በጨለማው ፡ ዓለም ፡ ስመላለስ
ተሰነካክዬ ፡ እንዳላለቅስ
መንገዴን ፡ አሳየኝ ፡ ብርሃን ፡ ሆነህ
ጽዮን ፡ አግባኝ ፡ እጄን ፡ ይዘህ
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ እጄን ፡ ያዘኝ

አዝ፦ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ እጄን ፡ ያዘኝ
የማልረባ ፡ ነኝ ፡ ኃይል ፡ የሌለኝ
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ እጄን ፡ ያዘኝ
የማልረባ ፡ ደካማ ፡ ነኝ

4. ሥጋ ፡ ለባሹን ፡ ሳይ ፡ በዐይኖቼ
ሰውን ፡ ይዤ ፡ ስሮጥ ፡ በእጆቼ
የተሰባበርኩት ፡ ቁስሌ ፡ አልሻረም
አንተው ፡ ያዘኝ ፡ ለዘለዓለም
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ እጄን ፡ ያዘኝ

አዝ፦ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ እጄን ፡ ያዘኝ
የማልረባ ፡ ነኝ ፡ ኃይል ፡ የሌለኝ
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ እጄን ፡ ያዘኝ
የማልረባ ፡ ደካማ ፡ ነኝ