ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው (Gena Eko New)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አዝ፦ ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ለዚህ ፡ ያደረሰኝ
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ እኔን ፡ ሰው ፡ ያረገኝ
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ነፍሴን ፡ የመለሳት
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ከጥፋት ፡ ያዳናት
ለዚህ ፡ ጌታ ፡ እሰግዳለሁ ፤ እቀኛለሁ ፤ እዘምራለሁ
የከበረ ፡ ስሙን ፡ ከዘለዓለም ፡ እሰክ ፡ ዘለዓለም ፡ ይመስገን ፡ እላለሁ

1. ተስፋዬን ፡ ቆርጬ ፡ ዝዬ ፡ ሳለሁ
ባዶውን ፡ መረቤን ፡ ከሩቅ ፡ ያየው
አትረፍርፎ ፡ የሞላው ፡ ባዶነቴን
በደስታ ፡ የለወጠው ፡ ሃዘኔን
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፤ ኢየሱስ ፡ ነው

አዝ፦ ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ለዚህ ፡ ያደረሰኝ
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ እኔን ፡ ሰው ፡ ያረገኝ
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ነፍሴን ፡ የመለሳት
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ከጥፋት ፡ ያዳናት
ለዚህ ፡ ጌታ ፡ እሰግዳለሁ ፤ እቀኛለሁ ፤ እዘምራለሁ
የከበረ ፡ ስሙን ፡ ከዘለዓለም ፡ እሰክ ፡ ዘለዓለም ፡ ይመስገን ፡ እላለሁ

2. ታንኳዬን ፡ ማዕበሉ ፡ ሲያናውጣት
በቃ ፡ ልጠፋ ፡ ነው ፡ ባልኩኝ ፡ ሰዓት
በማዕበሉ ፡ ላይ ፡ ተረማምዶ
ሕይወቴን ፡ ከጥፋት ፡ የታደጋት
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፤ ኢየሱስ ፡ ነው

አዝ፦ ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ለዚህ ፡ ያደረሰኝ
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ እኔን ፡ ሰው ፡ ያረገኝ
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ነፍሴን ፡ የመለሳት
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ከጥፋት ፡ ያዳናት
ለዚህ ፡ ጌታ ፡ እሰግዳለሁ ፤ እቀኛለሁ ፤ እዘምራለሁ
የከበረ ፡ ስሙን ፡ ከዘለዓለም ፡ እሰክ ፡ ዘለዓለም ፡ ይመስገን ፡ እላለሁ

3. ወደ ፡ ኤማሆስ ፡ መንገድ ፡ ስገሰግስ
ጠወላልጌ ፡ አይቶ ፡ ልደርቅ ፡ ስደርስ
አጠገቤ ፡ ደርሶ ፡ የመለሰኝ
በተስፋ ፡ ሕይወቴን ፡ ያደሰልኝ
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፤ ኢየሱስ ፡ ነው

አዝ፦ ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ለዚህ ፡ ያደረሰኝ
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ እኔን ፡ ሰው ፡ ያረገኝ
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ነፍሴን ፡ የመለሳት
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ከጥፋት ፡ ያዳናት
ለዚህ ፡ ጌታ ፡ እሰግዳለሁ ፤ እቀኛለሁ ፤ እዘምራለሁ
የከበረ ፡ ስሙን ፡ ከዘለዓለም ፡ እሰክ ፡ ዘለዓለም ፡ ይመስገን ፡ እላለሁ

4. የኀጢአት ፡ ቀንበሬን ፡ የሰበረው
የሞት ፡ ዕዳዬንም ፡ የከፈለው
ከእስራቴ ፡ ፈቶ ፡ ነጻ ፡ ያደረገኝ
ለክብሩ ፡ እንድቆም ፡ የመረጠኝ
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፤ ኢየሱስ ፡ ነው

አዝ፦ ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ለዚህ ፡ ያደረሰኝ
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ እኔን ፡ ሰው ፡ ያረገኝ
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ነፍሴን ፡ የመለሳት
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ከጥፋት ፡ ያዳናት
ለዚህ ፡ ጌታ ፡ እሰግዳለሁ ፤ እቀኛለሁ ፤ እዘምራለሁ
የከበረ ፡ ስሙን ፡ ከዘለዓለም ፡ እሰክ ፡ ዘለዓለም ፡ ይመስገን ፡ እላለሁ